Daily Weather Report 25 November 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደብረ ማርቆስ፣ ጎሬ፣ ማሻ፣ ጅማ፣ አርባምንጭ፣ ነገሌ፣ ፉጎሌቃ፣ ቡሬ፣ መንደር 7 ፣ ቅዳሜ ገበያ እና ኩሚ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በዶሎመና ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የምስራቅ አማራ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the southern and southeastern regions of the country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, Debre Markos, Gore, Masha, Jimma, Arbaminch, Negele, Fugoleka, Bure, Village 7,Kidame Gebeya and Kumi received light to moderate (1-29mm) rainfall, while Dolomena received heavy rainfall. On the other hand, the northern, central, northeastern and eastern parts of the country have experienced dry, sunny and windy bega weather. In addition, in some areas of East Amhara and the eastern highlands of the country, the daily minimum temperature has been recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ኖጎብ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ላይ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ እና ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና ምዕራብ ጎጃም ዞን በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedio zones of the Southern Ethiopia Region; Sidama Region zones, Somali Region Liben, Dawa, Afder, Shebele, Nogob, Jarar and Erer zones; Oromia Region West Arsi, Bale and East Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Also Jimma, Ilubabor, Buno Bedele and West and East Hararge zones. Bench Sheko, Sheka, Kefa, Dawro and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem liyu Zone, Kembata and Tembaro zones and West Gojam zone will experience light to moderate rainfall at some places. On the other hand, dry, sunny, and windy bega weather is expected in the northeast, central, and eastern parts of the country; forecast data indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius.