Daily Weather Report 25 November 06
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በላይበር፣ ጊዳአያና፣ ጊምቢ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጋምቤላ፣ ቡሬ፣ ጎሬ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላ፣ ወልቂጤ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ ሸንዲ፣ አሺ፣ ኩሚ፣ ሙጊ፣ ኦንጋ፣ መንደር 11 እና ቢላምቢሎ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በፉኝዶ፣ ኮበን፣ እርመጭ እና ጉበቲ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የምስራቅ አማራ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the southern and southeastern regions of the country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, in Leiber, Gidaayana, Gimbi, Nejo, Aira, Gambella, Bure, Gore, Wolayta Sodo, Dilla, Wolkite, Sati Gebeya, Shendi, Ashi, Kumi, Mugi, Onga, Village 11 and Bilambilo received light to moderate (1-29mm) rainfall, while Fugendo, Koben, Ermech and Gubeti received heavy rainfall. On the other hand, the northern, central, northeastern and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy bega weather. Additionally, in some areas of East Amhara and the eastern highlands of the country, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ላይ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ጅማ፣ ኢሉባቦር እና ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ የደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞን በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the bega, will have better cloud cover. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedio zones of the Southern Ethiopia Region; Sidama Region zones, Somali Region's Fafen, Liben, Dawa, Afder, Shebele, Korahe, Nogob, Jarar, Dolo and Erer zones; Oromia Region's West Arsi, Bale and East Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Also, Jimma, Ilubabor and West and East Hararge zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro; South Gondar, West Gojam and Awi zones will experience light rain in some areas. On the other hand, dry, sunny, and windy bega weather is expected in the northeastern, central, and eastern parts of the country; forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius.