Daily Weather Report 25 November 05

Weather Summary for previous day

Nov. 4, 2025

በትናንትናዉ ዕለት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቻግኒ፣ ፓዌ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ ፉኝዶ፣ አሽ፣ ጉበቲ፣ ሙጊ፣ መንደር-11፣ መንደር-13፣ ትንሹ ሜጢ እና ይርጋለም ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የምስራቅ አማራ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a cloud cover over the south and southeast parts of the country, which are in their second rainy season of the Bega, as well as in the western and southwestern areas of the country. In this regard, In Chagni, Pawe, Nekemte, Arjo, Fugnido, Ashi, Gubeti, Mugi, Village-11, Village-13, Tinshu Meti, and Yirgalem, light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded. Conversely, dry, sunny, and windy summer conditions were prevailed in the northern, central, northeastern, and eastern regions of the country. Additionally, in certain areas of eastern Amhara and the eastern highlands daily minimum temperatures was recorded below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Nov. 6, 2025

በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ዶሎ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ የኢታንግ፣ አኝዋክና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ በምስራቅ አማራ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the Bega. In this regard, in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio zones; Sidama region zones; Somali region Liben, Shebelle, Afder, Korahe, Doolo, Jarar and Erer Zones; from Oromia region West Arsi, Bale and East Bale; Guji and West Guji, Borena and East Borena Zones will receive light rainfall. additionally, in Jimma; Ilubabor, , west, east and Kelem Wellega zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, Marrakech Special Zone, Hadia, Halaba, Yum Special Zone, Kembata and Tembaro Zones, Asossa and Maokomo Zones, Agnuwak, Itang and Majang Zones will receive light rainfall at a few places. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega weather is expected in the northeastern, central, and eastern parts of the country; and also the forecast information indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius in a few places of east Amhara and eastern parts of the country.