Daily Weather Report 25 November 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአይከል፣ ዳንግላ፣ ፓዌ፣ ማንኩሽ፣ ቡለን፣ ሸርኮሌ፣ አሶሳ፣ ቅዳሜገበያ፣ ቡልቲ፣ ጎሬ፣ ቢላምቢሎ እና ዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለባቸው ሲሆን፣ በጥቂት የምስራቅ አማራ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the south and southeast parts of the country, which are in their second rainy season of the Bega. as well as in the western and southwestern areas of the country. In this regard, in Aykel, Dangla, Pawe, Mankush, Bullen, Sherkole, Assosa, Kidame Gebeya, Bulti, Gore, Bilambilo, and Dilla received light to moderate (1-29mm) amount rainfall. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega conditions prevailed in the northern, central, northeastern, and eastern parts of the country, and in a few highland areas of eastern Amhara and eastern regions the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ዶሎ፣ ጃራር፣ ኤረር እና ፋፈን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሚ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ደቡብምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ እና ምስራቅ ሀረርጌ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ የአኝዋክ፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች እና ምዕራብ ጎጃም ዞን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ በአንዳንድ ደጋማ ስፍራወች ላይ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the Bega. In this regard, in the Southern Ethiopia region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio zones; all Sidama region zones; Somali region Liben, Shebele, Afder, Dawa, Korahe, Doolo, Jarar, Erer and Fafen Zones; Oromia region West Arsi, Bale and East Bale; Guji and West Guji, Borena and East Borena Zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. additionally, in Jimma; Ilubabor, Buno Bedele, west, east and Kelem Wellega, Arsi and East Hararge zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Marrakech Special Zone, Hadia, Halaba, Yum Special Zone, Kembata and Tembaro Zones, Asossa and Maokomo Zones, Angiwak, Itang and Majang Zones, and West Gojjam Zones will receive light to moderate rainfall at some places. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega weather is expected in the northeastern, central, and eastern parts of the country; numerical forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius in some areas.