Daily Weather Report 25 November 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአይከል፣ ሻሁራ፣ ዳንግላ፣ አሶሳ፣ ነጆ፣ ላሬ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ቡሬ፣ ብላቴ፣ ዲላ፣ ሞያሌ፣ አሺ፣ ሲቦ፣ መንደር11፣ ይርጋለም፣ ፉጎሌቃ እና መቱ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቅዳሜ ገበያ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the south and southeast as well as the west and west regions of the country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, in Aykel, Shahura, Dangla, Asosa, Nejo, Lare, Gambella, Fugendo, Bure, Blate, Dilla, Moyale, Ashi, Sibo, Morga11, Yirgalem, Fugoleka And they received light to moderate (1-29mm) rainfall, with heavy rainfall on Kidame Gebeya. On the other hand, the northern, central, northeastern and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy bega weather. In addition, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ላይ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለምና ምዕራብ ወለጋ እና ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ የማጃንግ ዞን፤ ሀረር፤ የደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞን በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ10 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions that are conducive to the formation of bega rains will be stronger in the southern and southeastern regions of our country. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedio zones of the Southern Ethiopia region; The zones of Fafen, Liben, Dawa, Afder, Shebele, Korahe, Nogob, Jarar, Dolo and Erer in the Somali region; and the zones of West Arsi, Bale and East Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji in the Oromia region will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Also Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horogudru, Kelem and West Wellega and West and East Hararge Zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta Zones; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro; Metekel, Maokomo, Asosa and Kamash Zones; Majang Zone; Harar; South and Central Gondar, West Gojam and Awi zones will experience light rain in some areas. On the other hand, the northeast, central and eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy bega weather; the daily minimum temperature will be recorded below 10 degrees Celsius, forecast data indicate.