Daily Weather Report 25 November 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ፣ አይከል፣ ሻምቡ፣ ቻግኒ፣ ሞጣ፣ ቡለን፣ ጊምቢ፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ቡሬ፣ ማሻ፣ ቴፒ፣ ሊሙገነት፣ ሳውላ፣ ምዕራብ አባያ፣ ዲላ፣ ቦሬ፣ አሺ፣ ኩሚ፣ ሙጊ፣ ኦንጋ እና ሲቦ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በአሶሳ፣ ቅዳሜ ገበያ እና ኮበን ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the southern and southeastern parts of the country, which are in their second rainy season of the bega, as well as the western and northwestern parts of the country. In this regard, in Debarq, Aykel, Shambu, Chagni, Mota, Bulen, Gimbi, Nekemte, Gore, Bure, Masha, Tepi, Limugenet, Saula, West Abaya, Dilla, Bore, Ashi, Kumi, Mugi, Onga and Sibo received light to moderate (1-29mm) rainfall, while Assosa, Saturday Market and Koben received heavy rainfall. On the other hand, the northern, central, northeastern and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy bega weather. Additionally, the lowest temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ሸበሌ፣ ፋፈን፣ አፍዴር፣ ዳዋ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ እና ኤረር ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሚ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት የጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፤ አርሲ ዞኖች፣ የአሶሳ፣ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የአኝዋክና ማጃንግ ዞኖች፤ የማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ10 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions that are conducive to the occurrence of bega rains will have cloud cover over the southern and southeastern regions of our country. In this regard, the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio zones of the Southern Ethiopia Region; All zones of Sidama Region; Liben, Shebele, Fafen, Afder, Dawa, Korahe, Nogob and Erer zones of Somali Region; West Arsi, Bale and East Bale zones of Oromia Region; Guji and West Guji, Borena and East Borena zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Additionally, due to the prevailing cloud cover, the following zones are expected to experience rainfall: Jimma; Ilubabor, Kelem Wellega, East and West Hararge; Arsi zones; Assosa, Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem liyu Zone, Kembata and Tembaro zones; Anwak and Majang zones; Central and West Gondar and West Gojam zones in some places. On the other hand, dry, sunny and windy bega weather will be observed in the northeastern, central and eastern parts of the country; forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 10 degrees Celsius.