Daily Weather Report 25 November 01

Weather Summary for previous day

Oct. 31, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ፣ ጎንደር፣ ሻሁራ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ አይራ፣ ጨዋቃ፣ ጋምቤላ፣ ማሻ ፣ ቴፒ፣ ጂንካ፣ አሺ፣ ጉበቲ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ ኩሚ፣ ሙጊ፣ ኦቦመሪጋ፣ ሲቦ እና ትንሹ ሜቲ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በ አማን ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a cloud cover over the southern and southeastern parts of the country, which are in their second rainy season of the bega, as well as the western and northwestern parts of the country. In this regard, in Debarq, Gondar, Shahura, Dangla, Chagni, Aira, Saltuka, Gambella, Masha, Tape, Jinka, Ashi, Gubeti, Kidame Gebeya, Kumi, Mugi, Obomeriga, Sibo and Tinshu Meti received light to moderate (1-29mm) rainfall, while Amman received heavy rainfall. On the other hand, the northern, central, northeastern and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy bega weather. In addition, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.,

Weather Forecast for next day

Nov. 2, 2025

በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ሸበሌ፣ አፍዴር፣ ዳዋ እና ኤረር ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሚ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የአሶሳ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ የአኝዋክ፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች፤ የማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በመንገሽ፣ ጎደሬ፣ ሸኮ፣ ማሻ፣ ሳሌ ኖኖ፣ ገሻ፣ ጨና፣ የኪ እና ቦንጋ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ በጥቂት የምስራቅ አማራ አከባቢዎች የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ10 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, in the Southern Ethiopia Region, Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio zones; All Sidama Region zones; Somali Region Liben, Shebele, Afder, Dawa and Erer Zones; Oromia Region West Arsi, Bale and East Bale; Guji and West Guji, Borena and East Borena Zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Also, Jimma; Ilubabor, Kelem Wellega, Arsi, East and West Hararge; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem liyu Zone, Kembata and Tembaro zones; Asosa, Metekele and Maokomo zones; Anwak, Itang and Majang zones; Central and West Gondar and West Gojam zones will receive light to moderate rainfall at some places. Also, based on the intensifying weather events, Mengesh, Godere, Sheko, Masha, Sale Nono, Gesha, Chenna, Yeki and Bonga will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, dry, sunny, and windy bega weather is expected in the northeastern, central, and eastern parts of the country; numerical forecast indicate that the daily minimum temperature will be recorded below 10 degrees Celsius in some areas of eastern Amhara.