Daily Weather Report 25 May 29
Weather Summary for previous day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ በሰሜን፣በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣በመካከለኛው፣በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፣ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኽምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፤ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምስራቅ ትግራይ፣በምዕራብ ሸዋ፣ከፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ መተሐራ፣ቋራ፣ ድሬዳዋ፣ ሰመራ፣ዳሊፋጌ፣ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, weather conditions favorable for rainfall will continue to intensify across the western, northern, northwestern, northeastern, central, eastern, and southern parts of our country. Consequently, in the western, northern, central, southern, eastern, and southeastern zones of the Tigray region; in the western, northern, central, and southern Gondar including, Awi zone, western and eastern Gojjam, Wag Hemra, and northern Shewa the special zones of the Oromo Ethic, northern and southern Wollo zones of the Amhara region; the Bench Sheko, Sheka, Keffa, Konta, western Omo, and Dawuro zones in the southwestern Ethiopia region; the Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, Gedeo, Kora, southern Omo, and Gedeo zones in the southern Ethiopia region; the Guji and western Guji, Borena and eastern Borena, Bale and eastern Bale, Arsi and western Arsi, eastern and western Hararghe, Jimma, Ilubabor, Buno Bedelle, Kelem, Horo Guduru, western and eastern Wollega, and northern and eastern Shewa zones in Oromia region; Addis Ababa; Sidama region zones; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, and Yem special zones in the central Ethiopia region; the Kambata and Tembaro zones; the Agnuwak, Nuer, Majang, and Itang zones in the Gambela region; and the Metekel, Asosa, Kamashi, and Mao Komo zones in the Benishangul-Gumuz region. These areas will receive rainfall ranging from light to moderate intensity (1-29 mm).In addition, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is expected in the eastern Tigray, western Shewa, Keffa, and western Omo zones. On the other hand, in Humera, Metema, Metehara, Quara, Dire Dawa, Semera, Dallifage, Dubti, Gewane, Elidar, Awash Arba, Ayshe, and Gode, daytime temperatures are forecasted to exceed 38 degrees Celsius, according to our weather forecast.
Weather Forecast for next day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን በምዕራብ፣በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ ማዕከላዊ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ በምዕራብ፣ ሰሜን ፣ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር እና ቡኖበደሌ ዞኖች እንዲሁም አዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ዳሊፋጌ፣አዋሽ አርባ፣ ድሬዳዋ፣መተሐራ፣ጎዴ እና ፉኝዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.8 እስከ 45.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there were cloudy conditions in the western, northwestern, northern, northeastern, central, and southern parts of our country. Additionally, related rainfall was recorded in the southern central and eastern zones of Tigray; in the western, northern, central, and southern parts of Gondar; the Awi zone; the western and eastern zones of Gojjam; the Wag Hemra zones; the Kelem, western, eastern, and Horogudru Wollega zones; Jimma; Ilu babor; and Bunno Bedele zones. Likewise, Addis Ababa experienced light to moderate rainfall. On the other hand, high daytime temperatures ranging from 35.8 to 45.0 degrees Celsius were recorded in Semera, Gewane, Dallifage, Awash Arba, Dire Dawa, Metehara, Gode, and Fugnido.