Daily Weather Report 25 May 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞን፤ በምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች፤ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፤ ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ጉራጌ፣ ስልጤ እና ሀድያ ዞኖች፤ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ወላይታ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በባህርዳር፣ አንገርጉትን፣ ጨዋቃ፣ ወላይታ ሶዶ እና አርባምንጭ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በባቲ፣ ፉኝዶ፣ ኑራኢራ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ አይሻ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ ጭፍራ፣ ዳሊፋጌ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-46.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the western, northwestern, northeastern, central, southern and southwestern parts of our country. In this regard, there was also a cloud cover in the southeastern Tigray zone; in the western, northern, central and southern Gondar, Awi zone, western and eastern Gojam, Waghemra and northern Wollo zones. Oromo Nationality Special Zone; Kelem, West, East and Horogudru, Wellega, Jimma, Ilubabor, Bunobdele, West and South West Shewa and West Arsi zones; Addis Ababa; Gurage, Silte and Hadiya zones; Sheka, Bench Sheko and Wolaita zones received light to moderate rainfall. Additionally, Bahir Dar, Angerugut, Chewaka, Wolaita Sodo and Arbaminch received heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, in Bati, Fugendo, Nuraira, Semera, Gewane, Awash Arba, Aisha, Diredawa, Metahara, Chafra, Dalifage and Gode, the maximum temperature of the day was recorded at 35.0-46.2 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ አንፃራዊ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኽምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በመተከል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ሰመራ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions favorable for rain formation will be relatively strong in the western half, southern, central, northeastern and eastern parts of our country. In this regard, the zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro in the southwestern region of Ethiopia; the zones of Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo and Gedio in the southern region of Ethiopia; ; From the Oromia Region, Guji and West Guji, Bale, Arsi and West Arsi, East and West Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horo Guduru, West and East Wellega, West, Southwest, North and East Shewa Zones; Addis Ababa; Harar; Sidama Region Zones; From the Central Ethiopia Region, Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; The Anuak, Majang and Itang zones of Gambella region; the Metekal, Asosa, Kamash and Maokomo zones of Benishangul Gumuz region; the West, North, Central and South Gondar, Awi zone, West and East Gojam, Waghemra, North Shewa, North and South Wollo zones of Amhara region; the West, North West, Central, South, East and South East zones of Tigray region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, Metekel, Horo Guduru, Wellega, West Shewa, Sheka and Kefa zones will experience heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, statistical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will be recorded above 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Semera, Awash Arba, Gewane and Aisha.