Daily Weather Report 25 May 27
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በማዕከላዊ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ በምዕራብ፣ ሰሜን ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች፤ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና አርሲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ጉራጌ እና ሀድያ ዞኖች፤ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ አኝዋክ እና ወላይታ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በነቀምቴ፣ ቴፒ፣ አይራ፣ በደሌ እና ጊምቢ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ አይሻ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ ጭፍራ፣ ዳሊፋጌ እና መተማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ37.8-45.6 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the western, northwestern, northeastern, central, southern, and southwestern parts of our country. In association with this, in the central, eastern, and southeastern zones of Tigray; western, north, central and south Gondar, Awi zone, western and eastern Gojjam, Waghemra, and northern Wollo zones; in the western, eastern, and Horogudru Wolga, Jimma, Ilubabor, Bunobedele, western and southwestern Shewa, and Arsi zones; Addis Ababa; Gurage and Hadiya zones; Sheka, Bench Sheko, Agnwak, and Wolayta zones received light to moderate amounts of rainfall. Additionally, in Nekemte, Tepi, Aira, Bedele and Gimbi experienced heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. Conversely, in Samara, Gewane, Awash Arba, Aisha, Dire Dawa, Metehara, Chifra, Dalifage and Metema the maximum temperature of the day ranged from 37.8 to 45.6 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኽምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ መተከል እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ሚሌ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚመዘገብ አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, the rain-giving weather events will intensify over the western half, southern, central, northeastern, and eastern parts of the country. In association with this, from the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo, and Dauro zones; from the Southern Ethiopia region Wolayta, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo, and Gedeo zones; from the Oromia region Guji and west Guji, Bale, Arsi and west Arsi, east and west Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, Horogudru, west and east Wellega and west, southwest, north, and east Shewa zones; Addis Ababa; Harar; Sidama regional zones; from the Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata, and Tembaro zones; from Gambella region Angwuak, Majang, and Itang zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Assosa, Kamash and Maokomo zones; from Amhara region west, north, central, and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, Waghemra, north Shewa, and north and south Wollo zones; and from Tigray region west, northwest, central, south, east, and southeast zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. Additionally, Awi zone, west Gojjam, central and south Gondar, Metekel, and west Shewa zones will receive heavy rainfall exceeding 30 mm within a 24-hour. Conversely, the numerical weather prediction indicates that the daily maximum temperature will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Funedo, Samera, Mille, Awash Arba, Gewane, and Aisha.