Daily Weather Report 25 May 26

Weather Summary for previous day

May 25, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ነጆ፣ ጊዳአያና፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ጎሬ፣ ሶኮሩ፣ ካቺሴ፣ ወሊሶ፣ ሆሳዕና፣ አማን፣ ቦሬ፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ ላይበር፣ አዴት፣ ባህርዳር፣ ሞጣ፣ ደብረወርቅ፣ ነፋስመዉጫ፣ ጎንደር፣ ደባርቅ፣ አይደር፣ መቀሌ፣ አድዋ እና አዲግራት ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአይከል እና በጅማ ከ30 በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ እና ቀብሪዳሃር ከ36.4-41.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage over the southwest, west, south, central, and northeast parts of our country. Consequently, Nedjo, Gidayana, Gatira, Chira, Gore, Sokoru, Kachise, Waliso, Hosaina, Aman, Bore, Chagni, Dangila, Laiber, Adet, Bahirdar, Motta, Debrework, Nefasmewcha, Gondar, Debark, Aider, Mekelle, Adwa, and Adigrat received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Besides, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Ayikel and Jimma. In contrast, the day's maximum temperature was recorded in Gambella, Fugnido, Metehara, Dire Dawa, Aisha, and Kebridehar, ranging from 36.4 to 41.5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

May 27, 2025

በነገው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን እና ፋፈን ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኽምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም መተከል፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በአቦቦ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ሚሌ፣ አዋሽ አርባ፣ ገዋኔ እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

For the upcoming day, cloud coverage is anticipated over the country's western half, southern, central, northeastern, and eastern parts. In this respect, from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Burji, Konso, Kore, Gardula, south Omo and Gedeo; from the Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale, Arsi and west Arsi, east and west Hararge, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, north, west, southwest and east Shewa zones; Addis Ababa; Harar; Sidama region zones; from Somali region Dawa, Liben and Fafen zones; from central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region Agnuak, Nuwer, Majang and Itang zones; from Benishangul Gumuz region Metekal, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from Amhara region north, west, central and south Gondar, Awi zone, west and east Gojjam, Waghemra, north and south Wollo zones; from Tigray region west, northwest, central, south and southeast zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Moreover, Metekel, Awi zone, west Gojjam, west and south Gondar, west and south west Shewa zones will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. Conversely, the maximum daily temperature will be recorded exceeding 38 degrees Celsius in Abobo, Gambella, Fugnido, Humera, Metema, Quara, Metekel, Semera, Mile, Awash Arba, Gewane, and Gode.