Daily Weather Report 25 May 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ መተማ፣ ጎንደር፣ መተከል፣ አሶሳ፣ አይራ፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ ካቺስ፣ ጨዋቃ፣ ጋምቤላ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ በደሌ፣ ጅማ፣ ማሻ፣ ሆሳዕና፣ ወሊሶ፣ እምድብር፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ተርጫ፣ ሳውላ፣ ቦሬ፣ ዲላ፣ ቡሌሆራ፣ ቡርጂ፣ ያቤሎ፣ አማን እና ማጂ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአየሁ፣ ነጆ፣ ጋቲራ፣ ጅንካ እና ጊኒር ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ ገዋኔ፣ መተማ፣ ጎዴ እና አዋሽ አርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38.2-41.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the northwest, west, central, south and southwestern regions of our country. In this regards, in Debark, Metema, Gondar, Metekel, Asossa, Aira, Shambhu, Nekemte, Kachis, Chewaka, Gambella, Gore, Chira, Bedele, Jimma, Masha, Hosanna, Woliso, Emdibir, Hawassa, Wolayta Sodo, Tercha, Sawla, Bore, Dilla, Bulehora, Burji, Yabelo, Aman, and Maji received light to moderate amounts of rain. Additionally, Ayehu, Nedjo, Gatira, Jinka, and Ginir experienced heavy rainfall exceeding 30 mm. On the other hand, in Fugnido, Dire Dawa, Metehara, Gewane, Metema, Gode, and Awasharba the maximum temperature reached 38.2 to 41.2 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈንና ጃራር ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ ካማሽ፣ መተከል፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ ጎንደር በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-41 ዲግሪ ሴልሺየስ ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, the rain formation weather events will continue to intensify across the Belg rainy seasons benefiting areas of our country, as well as in the north and northwest areas of the country. In association with this, from the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo, and Dawro zones; Gamo, Gofa, Basketo, Gardolla, Kore, South Omo, and Gedeo zones; from the Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata, and Tembaro zones; Sidama region zones; from Oromia Region Guji and east Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, west Arsi, west and east Hararge, west and Southwest Shewa, Jimma, Ilubabor, Horo Gudru, Kelem, east and west Wellega zones, Addis Ababa, and Harar; from Benishangul-Gumuz region, Metekel, Assossa, Kamash and Mao Como zones; from Gambella region Agnuak, Nuer, Itang and Majang zones; from Somali region Fafen and Jarrar zones, from Tigray region west and northwest zones; from Amhara region north, central and south Gondar, Awi, east and west Gojjam zones receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. Also in Assosa, Kamash, Metekel, Horo Gudru, west and east Wellega, Buno Bedele, west Shewa, and west Gondar within 24 hours there will be heavy amounts of rain over 30 mm. On the other hand, forecast data indicate that the maximum temperature of the day in Samara, Dubti, Gewane, Elidar, Awasharba, and Aisha will expect to range between 38 and 41 degrees Celsius.