Daily Weather Report 25 May 21

Weather Summary for previous day

May 20, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በዳንግላ፣ ሞጣ፣ የትኖራ፣ አሶሳ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ አንርጉትን፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ በደሌ፣ ኢጃጂ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ማጂ፣ ተርጫ፣ ወላይታ ሶዶ፣ እምድብር፣ ሰኮሩ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሐዋሳ፣ ቦሬ፣ ዲላ፣ ቡሌሆራ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ እና ነገሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በሻምቡ እና ካችስ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በጭፍራ፣ ድሬዳዋ፣ መተሐራ፣ ገዋኔ፣ ጋምቤላ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38.2-43.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the western, central, southern and southwestern parts of our country. In this regard, there were also clouds in Dangla, Motta, Yetnora, Asosa, Nejo, Aira, Gimbi, Anrguten, Nekemte, Gore, Chira, Jimma, Bedele, Ejaji, Ambo, Woliso, Addis Ababa, Addis Ababa, Tepi, Aman, Maji, Tercha, Wolaita Sodo, Emdbir, Sekoru, Hosanna, Warabe, Hawassa, Bore, Dilla, Bulehora, Burji, Konso and Negele received light to moderate rainfall, while Shambu and Kachis received heavy rainfall of more than 30 mm. On the other hand, Chafra, Dire Dawa, Metahara, Gewane, Gambella and Aisha recorded the highest daily temperature of 38.2-43.2 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

May 22, 2025

በነገዉ ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈንና ጃራር ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪ በአሶሳ፣ ካማሽ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ እና ፉኝዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-41 ዲግሪ ሴልሺየስ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow Our forecast data indicates that weather conditions favorable for rain will continue to strengthen in the western, central, southwestern, southern and northwestern regions of our country. In this regard, the zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dauro in the southwestern region of Ethiopia; the zones of Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo and Gedeo in the southern region of Ethiopia; From the Central Ethiopian Region, Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; Sidama Region Zones; From the Oromia Region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, West Arsi, West and East Hararge, West and South West Shewa, Jimma, Ilubabor, Horo Gudru, Kelem, East and West Wellega Zones; Addis Ababa; Harar; The Metekal, Asosa, Kamash and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; the Anuak, Nuer, Itang and Majang zones of Gambella region; the Fafen and Jarar zones of Somali region; and the North, Central and South Gondar, Awi, East and West Gojam zones of Amhara region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Assosa, Kamash, West and East Wellega, Buno and Dele will experience heavy rainfall of more than 30mm within 24 hours. On the other hand, Humera, Metema, Semera, Dubti, Gewane, Elidar, Awash Arba, Aisha, Gambella, Lare and Fugendo will record the highest temperature of the day between 38-41 degrees Celsius.