Daily Weather Report 25 May 2024

Weather Summary for previous day

May 25, 2024

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይበልጥ ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሆሮ ጉድሩና ቄለም ወለጋ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ቦረና፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ አዲስ አበባ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል ኑዌር፣ ኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ፤ ከሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ጌዴኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ እና ሸበሌ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ ትግራይ፣ ምዕራብ አማራ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሐረር ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክሉ፡፡

Tomorrow the Cloud cover and accumulation will continue to strengthen in the northwest, west, south, southwest and east areas of the country. Along with this, from Tigray region the west, northwest and central zones; Amhara region North, West, South and Central Gondar, Awi, West and East Gojam zones; From the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Horo Gudruna, Kelem Welega, Southwest, Northwest and East Showa, Borena, Arsi West Arsi, Guji West Guji, Bale, West and East Hararge zones; Harar; Addis Ababa; Plantation from Benshangul Gumuz region, Asosa and Mao Komo zones; from the Nuer, Itang, Anuwak and Majang zones of the Gambella Region; From South West Ethiopia Region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dawuro and West Omo Zones; From Central Ethiopia Gurage, Silte, Hadia, Kambata and Tembaro zones; All zones from Sidama region; From South Ethiopia region, Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, Amaro, Gedeo and South Omo zones; Somali region Fafen, Jarar, Erer, Nogob, Korahe and Shebele zones will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, to that in some areas of West Tigray, West Amara, West, East and South Oromia, South West Ethiopia and Harar zones, there will be more than 30 mm of heavy rain in 24 hours.

Weather Forecast for next day

May 26, 2024

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው። በመሆኑም ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ሰሜንና ምዕራብ ሸዋ ፣ ምስራቅና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ዳውሮ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ከምባታና ጠምባሮ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በተርጫ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the north-west, west, south and east of the country. Thus, from the Amhara region, the North, South and Central Gondar, West and East Gojam zones; From Oromia region Jimma, North and West Showa, East and Horo Gudru Wolega, East Hararge, Bale, Borena, Guji and West Guji zones; From South West Ethiopia Region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, Dauro and West Omo Zones; Sidama Region Zones; Gurage, Silte, Hadia, Kebatana and Tembaro zones of central Ethiopia region received light to moderate rains, while heavy rains of more than 30 mm were recorded in Tercha.