Daily Weather Report 25 May 20
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቻግኒ፣ ዳንግላ፣ መካነ ሰላም፣ የትኖራ፣ ሻምቡ፣ ካቺስ፣ ኢጃጂ፣ ጊምቢ፣ ነጆ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ጎሬ፣ ጋምቤላ፣ ቡሬ፣ ሰኮሩ፣ ሆሳዕና፣ ተርጫ፣ አማን፣ ማጂ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ፣ ብላቴ፣ ዲላ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ እና ሞያሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በጅማ እና ቦሬ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተሐራ፣ ቀብሪደሃር፣ አይሻ፣ ድሬዳዋ፣ ጨዋቃ፣ መተማ እና ጋምቤላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.8-41.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the western, central, southern and southwestern parts of our country. In this regard, in Chagni, Dangla, Mekane Selam, Yitnora, Shambu, Kachis, Ejaji, Gimbi, Nejo, Arjo, Bedele, Gatira, Chira, Gore, Gambella, Bure, Sekoru, Hosanna, Tercha, Aman, Maji, Saula, Jinka, Wolaita Sodo, Arbaminch, Bilate, Dilla, Bulehora, Negele and Moyale received light to moderate rainfall, while Jimma and Bore received heavy rainfall of more than 30 mm. On the other hand, in Metahara, Kebridehar, Aisha, Dire Dawa, Chewaka, Metema and Gambella, the maximum daily temperature was recorded at 35.8-41.2 degrees Celsius
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ ፣ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ፋፈንና ጃራር ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪ በሸካ፣ ከፋ እና ቤንች ሸኮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡በሌላ በኩል በመተማ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ እና ፉኝዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-41 ዲግሪ ሴልሺየስ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow Weather conditions favorable for rain formation will be stronger in the western, central, southwestern, southern and northwestern regions of our country. In this regard, the zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dauro in the southwestern region of Ethiopia; the zones of Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo and Gedeo in the southern region of Ethiopia; From the Central Ethiopian Region, Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; Sidama Region Zones; From the Oromia Region, Guji and West Guji, Borena and East Borena, Bale, West Arsi, East Hararge, West and South West Shewa, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Gudru, Kelem, East and West Wellega Zones; From the Benishangul Gumuz Region, Metekel, Asosa, Kamash and Mao Komo Zones; The Anuak, Nuer, Itang and Majang zones of Gambella region; the Fafen and Jarar zones of Somali region; and the North, Central and South Gondar, Awi, East and West Gojam zones of Amhara region will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, our forecast data indicates that Sheka, Kefa and Bench Sheko will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperatures in Metema, Metekel, Semera, Dubti, Gewane, Elidar, Awash Arba, Aisha, Gambella, Lare and Fugendo will be recorded between 38-41 degrees Celsius.