Daily Weather Report 25 May 17

Weather Summary for previous day

May 16, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአዴት፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ አይራ፣ ጋምቤላ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ አርባምንጭ፣ ቡሌሆራ እና ቦሬ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ሸርኮሌ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ጋምቤላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35--41.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the southern and western regions of our country. In this regards, in Adet, Shambu, Nekemte, Arjo, Aira, Gambella, Gore, Chira, Jimma, Arba Minch, Bulehora, and Bore received light to moderate (1 to 29 mm) amount of rainfall. On the other hand, in Metema, Sherkole, Metehara, Dire Dawa, Gode, and Gambella recorded the highest temperature of the day, reaching 35 to 41.5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

May 18, 2025

በነገዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ እንዲሁም ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር እና አዊ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ እና ፉኝዶ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover in the southern, southwestern, western, and northwestern parts of our country. In association with this, from Southern Ethiopia region Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo, and Gedeo zones; from southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo, and Dauro zones; from Oromia region west Guji and Guji, Bale, Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Horogudru, Kelem, east and west Wellega zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; and from Benishangul-Gumuz region Metekel, Assossa, Kamash, and Mao Como zones; from Amhara region west Gondar and Awi zones will receive light rainfall. On the other hand, numerical forecast data indicate that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Semera, Dubti, Gewane, Elidar, Awasharba, Aiysha, Gambella, Lare, and Fugnido.