Daily Weather Report 25 May 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቻግኒ፣ አዴት፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ጊምቢ፣ ጋምቤላ፣ ጎሬ፣ ጨዋቃ፣ አርጆ፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጋቲራ፣ ኢጃጂ፣ ጊዳአያና፣ ሻምቡ፣ ሊሙገነት፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ማሻ፣ ሆሳዕና፣ አርሲ፣ ቦሬ፣ ዲላ፣ ቡሌሆራ፣ አመሮ፣ ቡርጂ እና ኮንሶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ሲሆን በአንገርጉትን እና ቡሬ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ አዋሽአርባ፣ መተሀራ፣ ፉኝዶ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ጎዴ እና ጋምቤላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35-44.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the southern and western parts of our country. In this regards, in Chagni, Adet, Bullen, Asossa, Gimbi, Gambella, Gore, Chewaka, Arjo, Nekemte, Bedele, Gatira, Ejaji, Gidayana, Shambu, Limugenet, Chira, Jimma, Masha, Hosanna, Arsi, Bore, Dilla, Bulehora, Amero, Burji, and Konso received light to moderate rainfall (1-29 mm), while in Angergut and Bure recorded heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, Semera, Awasharba, Metehara, Fugnido, Dire Dawa, Aisha, Gode, and Gambella recorded the highest temperature of the day, reaching 35 to 44.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የኤረር፣ ቆራሄ፣ ዶሎ እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እንዲሁም ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር፣ አዊ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southern, southeastern, southwestern, and western regions of the country. In association, in Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo, and Gedeo zones from the Southwest Ethiopia region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo, and Dauro zones; from Oromia region the west Guji and Guji, Bale, east and west Hararge, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Horogudru, Kelem, east and west Wellga zones; from Somali region Erer, Korahe, Doolo and Shebelle zones; from Gambella region Agnuak, Itang, and Majang zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Assossa, Kamash and Mao Komo zones; from Central Ethiopia region Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata, and Tembaro zones; and from Amhara region west Gondar, Awi, and west Gojjam zones are expected to receive light to moderate rainfall amounts (1-29 mm). On the other hand, in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Fugnido, Semera, Dubti, Gewane, Elidar, Awasharba and Aiysha the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius.