Daily Weather Report 25 May 15

Weather Summary for previous day

May 14, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ ቻግኒ፣ አዴት፣ ዳንግላ፣ ቡለን፣ ማንኩሽ፣ ነጆ፣ አቦቦ፣ ሻምቡ፣ ካቺስ፣ ነቀምቴ፣ ኢጃጂ፣ አምቦ፣ አዲስ አበባ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሀዋሳ፣ ኩሉምሳ፣ ቦሬ፣ አርባምንጭ፣ ዲላ፣ ቡሌሆራ እና ጃራ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ አዋሽአርባ፣ መተሀራ፣ ቀብሪደሃር፣ ጎዴ እና ጋምቤላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-43.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the southern, central and western parts of our country. In this regard, light to moderate (1-29 mm) rainfall was experienced in Debark, Chagni, Adet, Dangla, Bullen, Mankush, Nejo, Abobo, Shambu, Kachis, Nekemte, Ejaji, Ambo, Addis Ababa, Arjo, Bedele, Gore, Gatira, Chira, Emdbir, Hosanna, Warabe, Hawassa, Kulumsa, Bore, Arbaminch, Dilla, Bulehora and Jara. On the other hand, the highest daily temperatures in Samara, Awash-Arba, Metahara, Qebridhar, Gode and Gambella were recorded between 35.6-43.2 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

May 16, 2025

በነገዉ ዕለት በደቡብ ምስራቅ፤ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ሐረሪ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኤረር፣ ጃራርና ዶሎ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር፣ አዊ፣ ምዕራብ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ ሁኔታም ቀሪ የበልግ የግብርና ስራዎችነ ለማከናወን ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ ጅማ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ እና ጋምቤላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-41 ዲግሪ ሴልሺየስ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the southeast, southwest and west of our country. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo and Gedeo zones of the Southern Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; From the Oromia region, West Guji and Guji, Borena and East Borena, Bale and East Bale, East and West Hararge, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Bunobdele, Horogudru, Kelem, East and West Wellega, West and South-West Shewa zones; Harari; Sidama region zones; from the Somali region, Fafen, Erer, Jarar and Dolo zones; The Anuak and Majang zones of Gambella region; the Metekal, Asosa, Kamash and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, YEM liyu Zone, Kambata and Tembaro zones of Central Ethiopia region; and the West Gondar, Awi, West Gojam and North Shewa zones of Amhara region. Light to moderate rainfall (1-29 mm) is expected, which will be beneficial for the remaining belg agricultural activities. In addition, numerical forecast data indicates that Assosa, Jimma, Sheka and Kefa zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperatures in Metema, Quara, Metekel, Semera, Dubti, Gewane, Elidar, Awash Arba and Gambella will be recorded between 38-41 degrees Celsius.