Daily Weather Report 25 May 14

Weather Summary for previous day

May 13, 2025

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በምዕራብ እና መካከለኛ አማራ፣ በምዕራብ፣ ምስራቅ፣ መካከለኛና ደቡብ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ሲዳማ፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሆሳዕና፣ ማጂ፣ አርባምንጭ፣ ቡርጂ፣ ቡሌሆራ እና ጃራ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ እና ጋምቤላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-43.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a strong cloud cover over the areas of our country that benefited from the belg rains. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was received in the western and central Amhara, western, eastern, central and southern Oromia, central Ethiopia, Sidama, Benishangul Gumuz, Gambella, southern Ethiopia and southwestern Ethiopia regional zones. Additionally, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Hosanna, Maji, Arbaminch, Burji, Bulehora and Jara in 24 hours. On the other hand, in Samara, Gewane, Awash-Arba, Aisha, Metahara, Dire Dawa, Gode and Gambella, the maximum temperature of the day was recorded between 35.6-43.4 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

May 15, 2025

በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኤረር፣ ዳዋና ጃራር ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር፣ አዊ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38- 41 ዲግሪ ሴልሺየስ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second belg rainy seasons of our country. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo and Gedeo zones of the Southern Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; From the Oromia Region, West Guji and Guji, Borena and East Borena, Bale, East and West Hararge, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Bunobdele, Horogudru, Kelem, East and West Wellega, West and South West Shewa zones; Addis Ababa; Harari; Sidama Region zones; Fafen, Erer, Dawa, Jarar zones from Somali Region; Anuak and Majang zones from Gambella Region; Metekal, Asosa, Kamash and Mao Komo zones from Benishangul Gumuz Region; The Central Ethiopian Region's Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, YEM, Zone, Kambata and Tembaro Zones, and the Amhara Region's West Gondar, Awi and West Gojam Zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature in Humera, Metema, Quara, Metekel, Semera, Dubti, Gewane, Elidar, Awash Arba and Aisha will be between 38-41 degrees Celsius.