Daily Weather Report 25 May 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአርባምንጭ፣ ወላይታሶዶ፣ ዲላ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ እንድብር፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ነቀምቴ፣ ኢጃጅ፣ አምቦ፣ ፍቼ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ግራዋ፣ ሐሮማያ፣ ሐረር፣ አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ደብረታቦር፣ ደብረማርቆስ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ መተማ፣ ደባርቅ፣ መካነሰላም፣ ጉንዶመስቀል እና ሽሬእንደስላሴ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በሻምቡ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ፣ መተሀራ፣ ድሬዳዋ፣ ጎዴ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ እና መተማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.6-43.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the southern, southwest, eastern, central, west, and northwestern parts of our country. In this regards, Arba Minch, Wolaitasodo, Dilla, Konso, Burji, Indibir, Gore, Jimma, Nekemte, Ejaji, Ambo, Fiche, Bore, Negele, Moyale, Grawa, Haramaya, Harar, Addis Ababa, Bahir Dar, Debre Tabor, Debre Markos, Dangla, Chagni, Metema, Debark, Mekaneselam, Gundomeskel, and Shireendesilase received light to moderate rainfall (1-29 mm), while Shambu recorded heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. Additionally, in Samara, Gewane, Awasharba, Aiysha, Metehara, Dire Dawa, Gode, Gambella, Fugnido, and Metema the daily maximum temperatures was recorded ranging from 35.6 to 43.4 degrees Celsius for the day.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኤረርና ጃራር ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆንና የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ ኤሊዳር፣ አዋሽአርባ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage across the areas of our country that are the main and second rainy seasons of Belg, as well as in the western half of the country. In association with this, from the Southwest Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo, and Gedeo; from southwestern Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo, and Dawro zones; from the Oromia region west Guji, Guji, Borena, east Borena, Bale, east Bale, east and west Hararge, Arsi, west Arsi, Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Horogudru, Kelem, east and west Wellega and west, southwest, and east Shewa zones; Addis Ababa; Harari; from Somali region's Fafen, Erer, and Jarrar zones; from Gambella region Agnuak, Nuer, Itang, and Majang zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Asossa, Kamash, and Mao Como zones; from central Ethiopia Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata, and Tembaro zones; and from Amhara region west, north, south, and Central Gondar, Awi, and East and West Gojjam zones will receive light to moderate rainfall amounts (1-29 mm). The rainfall amount and distribution will be crucial for sustaining Belg agricultural activities. On the other hand, numerical forecast information indicate that the maximum temperature for the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Fugnido, Semera, Dubti, Gewane, Elidar, Awasharba, and Aiysha.