Daily Weather Report 25 May 12

Weather Summary for previous day

May 11, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሽሬ እንዳስላሴ፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ሻሁራ፣ ባህር ዳር፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ አየሁ፣ የትኖራ፣ አንገርጉትን፣ ሸርኮሌ፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ደምቢ ዶሎ፣ ጎሬ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ ጅንካ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ዲላ፣ ቡሌሆራ እና ዶሎመና ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ጋምቤላ፣ መተሐራ፣ ሚኤሶ፣ ድሬዳዋ፣ አይሻ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-40.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the northwest, south, southwest and west of our country. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was experienced in Shire Endasalasse, Debarq, Gondar, Shahura, Bahir Dar, Dangla, Chagni, Ayehu, Yetnnora, Angergut, Sherkole, Bulen, Asosa, Gambella, Dembi Dolo, Gore, Chira, Jimma, Jinka, Konso, Burji, Dilla, Bulehora and Dolomena. On the other hand, Gambella, Metahara, Mieso, Dire Dawa, Aisha, Kebridehar and Gode recorded daily high temperatures ranging from 35.2-40.0 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

May 13, 2025

በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የምዕራብ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ሀዲያ፣ ዳውሮ፣ ወላይታ እና ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ ፓዌ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-41 ዲግሪ ሴልሺየስ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg, as well as over the northern and northwestern regions of our country. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo and Gedeo zones of the Southern Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; West Guji and Guji, Borena and East Borena, Bale, East and West Hararge, West Arsi, Jimma, Ilubabor, Bunobdele, Horogudru, Kelem, East and West Wellega, West, South West and North Shewa zones from Oromia region; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Fafn, Nogob, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe and Dolo zones from Somali region; Anuwak, Nuer, Itang and Majang zones from Gambella region; The Metekel, Asosa, Kamash and Mao Komo zones of Benishangul Gumuz region; the Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, YEM Zone, Kembata and Tembaro zones of Central Ethiopia region; the West, North, South and Central Gondar, East and West Gojam and Awi zones of Amhara region and the West zone of Tigray region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, numerical forecast data indicates that heavy rainfall of more than 30 mm will occur in Illubabor, Jimma, Sheka, Kefa, Hadiya, Dawro, Wolayta, and West and East Hararge zones within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperatures in Humera, Metema, Quara, Pawe, Metekel, Gambella, Lare, Fugendo, Semera, Dubti, Gewane, Awash Arba and Aisha will be recorded between 38-41 degrees Celsius.