Daily Weather Report 25 May 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ጂንካ፣ ሳውላ፣ አርባምንጭ፣ ዲላ፣ ኮንሶ፣ አርጆ፣ ጎሬ፣ ጨዋቃ፣ ቡሬ፣ በደሌ፣ ነቀምቴ፣ ጊዳአያና፣ ቦሬ፣ ዶሎመና፣ ቡሌሆራ፣ መተሃራ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ሞጣ፣ ደብረታቦር፣ አይከል፣ ደባርቅ እና አምባማርያም ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ጨዋቃ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.2-36.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was strong cloud cover over the south, southwest, west and northwestern parts of our country. In this regards, in Jinka, Sawla, Arba Minch, Dilla, Konso, Arjo, Gore, Chewaka, Bure, Bedele, Nekemte, Gidayana, Bore, Bulehora, Metehara, Gambella, Abobo, Motta, Debretabor, Aykel, Debark and Amba Mariam received light to moderate amounts of rainfall (1-29 mm). On the other hand, in Gambella, Fugnido, Chewaka, Dire Dawa and Gode the maximum temperature of the day was recorded ranging from 35.2 to 36.4 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ፣ በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሸካ፣ ጅማ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ፣ ማኦ ኮሞ እና አሶሳ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over over areas of our country that are the main and second rainy seasons of Belg, as well as in the western, northern, and northwestern region. Concurrently, In association with this, from Southwest Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, South Omo, and Gedeo zones; from the Southwest Ethiopia area; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo, and Dauro zones; from Oromia region west Guji and Guji, Borena and east Borena, Bale, east and west Hararge, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Kelem, Horogudru, east and west Wellega, south west, west and north Shewa zones; from Somali region: Fafen, Nogob, Jarrar, Erer, Afder, Korahe, and Doolo zones; Sidama regional zones; from Central Ethiopia region Hadia, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Gambella region, Agnwuak, Nuer, Itang, and Majang zones; from Benishangul-Gumuz region Metekel, Asossa, Kamash, and Mao Como zones; from Amhara region south and west Gondar, Awi and west Gojjam zones, and from Tigray region northwest, west, central and eastern zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. Additionally, Sheka, Jimma, Kelem and west Wellega, Mao Como and Asosa zones there will be heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours. On the other hand, numerical forecast information indicates that the maximum temperature for the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Fugnido, Semera, Dubti, Gewane, and Awasharba.