Daily Weather Report 25 May 08
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂና ጌዲኦ ዞኖች ፤ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ጎንደር፣ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣አቦቦ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ እና ቀብሪዳሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the areas of our country that benefited from the belg rains. In this regard, Wolaita, Gamo, Gofa, South Omo, Konso, Burji and Gedio zones; Guji and West Guji, Bale, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, West, South West and East Shewa zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Sidama Region Zones; Bench Sheko, West Omo and Dawuro Zones; South Wollo, North Shewa, South Gondar, West and East Gojam Zones; North West, Central and South Tigray Zones received light to moderate rainfall (1-29 mm), while Addis Ababa recorded heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the highest daily temperatures in Gambella, Abobo, Semera, Gewane, Awash-Arba, Aisha and Kebridehar were recorded between 35.0-38.0 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ቤንችሸኮ፣ ሸካ፣ ምዕራብና ደቡብ ኦሞ እና ጉጂ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the main and second rainy seasons of the belg and the north western areas of our country. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Kore, South Omo and Gedeo zones of the Southern Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of the Southwestern Ethiopian Region; West Guji and Guji, Bale, Kelem and West Wellega, West, South West and East Shewa zones from Oromia Region; Addis Ababa; Harari; Dire Dawa; Liben, Afder and Shebele zones from Somali Region; Anuak and Majang zones from Gambella Region; Sidama Region zones; The North, South and Central Gondar, East and West Gojam, North Shewa, North and South Wollo zones of the Amhara region and the Northwestern zone of the Tigray region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, Bench sheko, Sheka, West and South Omo and Guji zones will experience heavy rainfall exceeding 30 mm in 24 hours. On the other hand, numerical forecast data shows that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Semera, Dubti, Gewane and Awash Arba.