Daily Weather Report 25 May 07

Weather Summary for previous day

May 6, 2025

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንከራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጅና ጌዲኦ ዞኖች ፤ በቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ሊበን እና ፋፈን ዞኖች፤ ጋቢ ዞን፤ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ጎንደር እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአቦምሳ፣ ቁሉቢ፣ አዳማ፣ ሾላገበያ፣ ቢሾፍቱ፣ ሀዋሳ፣ ብላቴ እና ቡሌሆራ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ እና አይሻ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-38.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was strong cloud cover over the Belg benefiting areas of our country. In this regards, Wolayta, Gamo, Gofa, South Omo, Konso, Burj and Gedeo zones; Borena and east Borena, Guji and west Guji, Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, west, southwest and east Shewa zones; Addis Ababa, Harar, Dire Dawa; Sidama regional zones; Sheka, Bench Sheko, west Omo and Dauro zones; Liben and Fafen zones; Gabi zone; south Wollo, north Shewa, south Gondar and east Gojjam zones received light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, in Abomasa, Kulubi, Adama, Sholagebeya, Bishoftu, Hawassa, Bilatte and Bulehora, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in 24 hours. On the other hand, in Gambella, Fugnido, Semera, Gewane, Awasharba and Aiysha, the maximum temperature of the day was recorded between 35.0-38.0 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

May 8, 2025

በነገዉ ዕለት ዝናብ ሰጪ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠን እና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እና ለአርብቶ አደር አካባቢዎችም ለእንስሳት መኖና ለመጠጥ ውሀ አቅርቦት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ቤንችሸኮ፣ ሸካ፣ ኮንታ፣ ምዕራብና ደቡብ ኦሞ፣ ጉጂ እና ባሌ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Tomorrow, the rainy weather events will continue in the main and second Belg rainy seasons benefiting areas of our country, as well as in the north and northwest areas of the country. In association with this, from the Southwest Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardolla, Kore, South Omo and Gedeo; Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; west Guji and Guji, Bale and east Bale, east and west Hararge, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Kelem and west Wellega, west, southwest and east Shewa zones; Addis Ababa, Harari, Dire Dawa; from Somali region Fafen, Nogob, Dawa, Liben, Jarrar, Erer, Afder, Shebelle, Korahe and Doolo zones; from Gambella region Agnwuak and Majang zones; zones of Sidama region; from Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; from Amhara region north, south and central Gondar, east and west Gojjam, north Shewa, north and south Wollo zones, and from Tigray region northwest, west, central and eastern zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall, while the rainfall amount and distribution will be of great importance for carrying out Belg agricultural activities and for pastoral areas for animal feed and drinking water availability. In addition, in Benchsheko, Sheka, Konta, west and south Omo, Guji and Bale zones received heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, based on the numerical weather prediction the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Fugnido, Semera, Dubti, Gewane and Awasharba.