Daily Weather Report 25 May 06
Weather Summary for previous day
ባለፉት ሁለት ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጅና ጌዲኦ ዞኖች ፤ በቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ጅማ፣ ቡኖበደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ኢታንግ ዞን፤ ኮንታ ዞን፤ ሊበን፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ ጃራር፣ ፋፈን እና ሲቲ ዞኖች፤ አውሲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግኸምራ፣ ደቡብና ሰሜን ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስረቅ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሽላቦ፣ ስሪንቃ፣ አዲስ አበባ፣ ኩልምሳ፣ መተሀራ፣ ደሎመና እና ያቤሎ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽአርባ፣ አይሻ እና ቀብሪደሀር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35.0-42.0 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
In the last two days, there was cloud cover over the belg benefiting areas of our country, as well as the northwestern parts of the country. In this regards, Wolayta, Gamo, Gofa, south Omo, Konso, Burj and Gedeo zones; Borena and east Borena, Guji and west Guji, Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, west, southwest and east Shewa, Jima, Bunobedele, Ilubabor, west, east and Horogudru Wellega zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; Sidama regional zones; Itang zone; Konta zone; Liben, Korahe, Shebelle, Jarrar, Fafen and Siti zones; Awsie and Gabi zones; north and south Wollo, north Shewa, Waghemra, south and north Gondar, Awi zone, west and east Gojjam zones; east, southeast, south and central Tigray zones received light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall. In addition, heavy amounts of over 30 mm were recorded in Shilabo, Sirinka, Addis Ababa, Kulumsa, Metehara, Delomana and Yabelo within 24 hours. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded 35.0-42.0 degrees Celsius in Metema, Gambella, Fugnido, Semera, Gewane, Awasharba, Ayesha and Kebridehar.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ የሚያገኙ ሲሆን፤ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭትም የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናውን ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም በቡኖበደሌ፣ ጅማ፣ ቤንችሸኮ፣ ሸካ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow there will be strong cloud cover and accumulation over areas of our country that are the main and second rainy seasons of Belg, as well as in the north and northwest areas of the country. In association with this, from Southwest Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Kore, South Omo and Gedeo; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from Oromia region west Guji and Guji, Bale and east Bale, east and west Hararge, Arsi and west Arsi, Jimma, Ilubabor, Kelem, Horogudru, east and west Wellega, west, southwest, north and east Shewa zones; Addis Ababa, Harari, Dire Dawa; from Somali region Siti, Fafen, Nogob, Dawa, Liben, Jarrar, Erer, Afder, Shebelle, Korahe and Doolo zones; from Gambella region Agnwuak and Majang zones; zones of Sidama region; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; from Amhara region north, south and central Gondar, Awi, east and west Gojjam, Waghemra, north Shewa, north and south Wollo zones and from Tigray region northwest, central, southeast and east zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of rainfall, and the rainfall amount and distribution will be of great importance for carrying out Belg agricultural activities. In addition, Bunobedele, Jimma, Bench Sheko, Sheka, west Omo, Wolaita, Gamo, Gofa and South Omo zones will receive heavy amounts of rainfall of more than 30 mm that could cause instant flooding within 24 hours. On the other hand, the maximum temperature for the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Fugnido, Semera, Dubti, Gewane and Awasharba.