Daily Weather Report 25 May 04

Weather Summary for previous day

May 3, 2025

በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብ፣ መካከለኛና ምስራቅ አማራ፤ በምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ በጋምቤላ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በደቡብ ሶማሌ፤ በሲዳማ፣ በሐረር እና በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በፅፅቃ፣ ደ/ማርቆስ፣ ሻምቡ፣ ካቺስ፣ ምዕራብ አባያ፣ ቦሬ እና ሽላቦ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በጋምቤላ፣ መተሀራ፣ ፉኝዶ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ ከ35.0-38.3 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had a cloud cover in the areas of our country that are the main and second rainy seasons of Belg. Along with this, West, Central, and East Amhara; West, Central, South, and East Oromia; Gambella; Southern Ethiopia; Southwestern Ethiopia; Central Ethiopia; Southern Somali; Sidama, Harar, and Addis Ababa light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Tsitsika, D/Markos, Shambu, Kachis, West Abaya, Bore, and Shelabo. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Gambella, Metahara, Fugendo, Dire Dawa, and Gode between 35.0-38.3 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

May 5, 2025

በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ዝናብ ሰጪ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ይበልጥ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፣ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ዋግኸምራ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ፋንቲ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ማሂ እና ሀሪ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ፣ ምስራቅና ማዕከላዊ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጅማ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the coming two days, rainy weather events will intensify in the main and second rainy seasons of the Belg, as well as in the northern and northwestern parts of the country. In line with this, from the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Kore, South Omo and Gedio zones; from the Southwestern Ethiopian Region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; from the Oromia Region, West Guji and Guji, Bale and East Bale, East and West Hararge, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor,Buno Badele, Kelem, Horo Gudru, East and West Wollega, West, South West and North Shewa zones; Addis Ababa; Harari, Dire Dawa; from the Somali Region Siti, Fafen, Nogob, Liben, Dawa, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe and Dolo zones; the zones of Sidama Region; from Gambella Region Anuak, Nuwer, Itang and Majang zones, from the the zones of Gurage, Silte, Hadiya, Membeed Zone, Kembata and Tembaro from the Central Ethiopia Region; from the Benishangul Gumuz Region  Metekel, Asosa, Kamash and Mao Komo zones, from the Amhara region West, north, South and Central Gondar, Awi, Waghemra, East and West Gojam and north shewa zones; from Afar region Kelbet, Fanti, Awsi, Gabi, Mayi and Hari zones and from Tigray region  North West, south, east and Central zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, Jimma, West Wellega, West and East Shewa, East and West Gojam, Sheka, Bench Sheko, Gurage, Silte, and Hadiya zones will receive heavy rainfall that may cause flash floods within 24 hours