Daily Weather Report 25 May 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምዕራብና መካከለኛ አማራ፤ በምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ ጋምቤላ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ፤ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በጅማ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በጋምቤላ፣ መተሀራ፣ ሚኤሶ፣ ድሬዳዋ እና ጎዴ ከ35.0-38.7 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had a cloud cover in the areas of our country which are the main and second rainy season of Belg. In line with this, West and Central Amhara; West, Central, South and East Oromia; Gambella; Southern Ethiopia; Southwestern Ethiopia; Central Ethiopia and Sidama light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded while heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Jimma. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Gambella, Metahara, Mieso, Dire Dawa and Gode between 35.0-38.7 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋና የተጠናከረ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፣ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኖጎብ፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ዋግኸምራ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ከአፋር ክልል የፋንቲ፣ አውሲ፣ ጋቢ፣ ማሂ እና ሀሪ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ሸካ፣ መተከል፣ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
For the following day, there will be widespread and strong cloud cover over the main and second rainy seasons of the Belg, as well as over the northern and northwestern regions of the country. In this regard, from the Southern Ethiopian Region, Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Kore, South Omo and Gedio zones; from the Southwestern Ethiopian Region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; from the Oromia Region, West Guji and Guji, Bale and East Bale, East and West Hararge, Arsi and West Arsi, Jimma, Illubabor, Kelem, Horo Gudru, East and West Wollega, West, South West and North Shewa zones; Addis Ababa; Harari, Dire Dawa; from the Somali Region Siti, Fafen, Nogob, Liben, Dawa, Jarar, Erer, Afder, Shebele, Korahe and Dolo zones; the zones of Sidama Region; from Gambella Region Anuak, Nuwer, Itang and Majang zones, from the the zones of Gurage, Silte, Hadiya, Membeed Zone, Kembata and Tembaro from the Central Ethiopia Region; from the Benishangul Gumuz Region Metekel, Asosa, Kamash and Mao Komo zones, from the Amhara region West, North, South and Central Gondar, Awi, Waghemra, East and West Gojam zones; from Afar region Fanti, Awsi, Gabi, Mayi and Hari zones and from Tigray region North West, West and Central zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, Kelem Wellega, Illubabor, Sheka, Metekel, and West Shewa zones will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the maximum temperature of the day will be recorded above 38 degrees Celsius in Humera, Semera, Dubti, Gewane and Awash Arba.