Daily Weather Report 25 May 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በማዕከላዊ እና ደቡብ ትግራይ፣ መካከለኛና ምስራቅ አማራ፤ በምዕራብ፣ መካከለኛ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ ጋምቤላ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ፤ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በወላይታ ሶዶ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በፉኝዶ፣ ጋምቤላ፣ መተሀራ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ ከ38.0-42.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the belg main and second rainy seasons of our country. Along with this, there was rain in Central and South Tigray, Central and East Amhara; West, Central, South and East Oromia; Gambella; Southern Ethiopia; Southwestern Ethiopia; Central Ethiopia and Sidama received light to moderate (1-29 mm) rainfall, while Wolaita Sodo received heavy rainfall of over 30 mm. On the other hand, the highest daily temperatures were recorded in Fugendo, Gambella, Metahara, Semera, Gewane and Awash Arba between 38.0-42.4 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ዝናብ ሰጪ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች እንዲሁም በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረሪ፤ ድሬዳዋ፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ኖጎብ፣ ዳዋ፣ ጃራር፣ ኤረር፣ አፍዴር፣ ሸበሌ እና ቆራሄ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን እና ከምባታ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ ከአፋር ክልል የፋንቲ እና ሀሪ ዞኖች እና ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ምስራቅ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ሸካ፣ መተከል፣ ምዕራብ ጎንደር እና ቡኖበደሌ ዞኖች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ ሰመራ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ እና አዋሽአርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow Our forecast indicates that rainy weather events will intensify in the areas of our country that experience the main and second rainy seasons of the belg, as well as in the northern and northwestern regions of the country. In this regard, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Kore, South Omo and Gedio zones of the Southern Ethiopian Region; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dauro zones of the Southwestern Ethiopian Region; From the Oromia Region, West Guji and Guji, Bale, East and West Hararge, Arsi and West Arsi, Jimma, Ilubabor, Kelem, Horogudru, East and West Wellega, West, South West and East Shewa zones; Addis Ababa; Harari; Dire Dawa; From the Somali Region, Fafen, Nogob, Dawa, Jarar, Erer, Afder, Shebele and Korahe zones; The zones of Anuak, Itang and Majang from Gambella Region; the zones of Sidama Region; the zones of Gurage, Hadiya, Membeed Zone and Kambata from Central Ethiopia Region; the zones of Metekel, Asosa, Kamash and Mao Komo from Benishangul Gumuz Region; the zones of West, North, South and Central Gondar, Awi, East and West Gojam, Waghemra, North and South Wollo from Amhara Region, Fanti and Hari zones of Afar region and Northwestern, Western, Central and Eastern zones of Tigray region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, Ilubabor, Jimma, Sheka, Metekel, West Gondar and Bunobdele zones will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Qara, Semera, Dubti, Gewane and Awash Arba.