Daily Weather Report 25 Mar 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በላሊበላ፣ ጨፋ፣ እንዋሪ፣ አሶሳ፣ ፉኝዶ፣ ካችስ፣ ጅማ፣ ጎሬ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ወሊሶ፣ አዲስ አበባ፣ ቡኢ፣ ቦሬ፣ ሐዋሳ፣ እምድብር፣ ወላይታ ፣ ወራቤ፣ ተርጫ፣ አርባምንጭ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ፣ ብላቴ፣ ያቤሎ፣ ሒርና፣ ግራዋ፣ ጅግጅጋ፣ ኩርፋጨሌ፣ ጨለንቆ፣ ድሬዳዋ እና ሐረር ከቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በሆሳዕና እና ቡሌሆራ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል ፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጋምቤላ እና ፉኝዶ ከ38-42.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there was a cloud cover over the areas of our country that benefited from the Belg rains. In connection with this, light to moderate rain was recorded in Lalibela, Chefa, Enwari, Asosa, Fugendo, Kachis, Jimma, Gore, Bedele, Chira, Woliso, Addis Ababa, Bui, Bore, Hawassa, Imdibir, Wolaita, Warabe, Tercha, Arbaminch, Saula, Jinka, Konso, Bilate, Yabelo, Hirna, Girawa, Jigjiga, Kurfachele, Chelenko, Dire Dawa and Harar. Additionally, heavy rainfall of over 30 mm was recorded in Hosanna and Bulehora. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded in Samara, Gewane, Awash Arba, Gambella and Fugendo between 38-42.5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ከመጠናከራቸዉ ጋር በተያያዘ በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ፣ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና አዊ ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ሆሩጉድሩ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ እና ባሌ ዞኖች፤ ድሬዳዋ፣ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክና ማጃንግ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች ፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ኖጎብ፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ፣ እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና የስራ እንቅስቃሴን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ላሬ፣ ገዋኔ፣ በቀብሪደሃር እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡
Tomorrow, due to the strengthening of weather conditions conducive to the occurrence of Belg rains, there will be cloud cover over the north, northwest, west, southwest and east of our country. In connection with this, the west and northwest of Tigray region, the west, central, north and south of Gondar, west and east of Gojam and Awi zones of Amhara region; From the Oromia region: Jimma, Buno Bedele, Ilubabor, Horugudru, East and West Hararge, Kelem, West and East Wellega, Guji and West Guji and Bale zones; Dire Dawa, Harar; from the Benishangul Gumuz region: Metekel, Asosa and Mao Komo; from the Gambella region: Anuak and Majang; from the Southwestern Ethiopia region: Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro; The Gofa, Basketo, Konso and Burji zones of the Southern Ethiopian Region, the Sidama Region zones, and the Fafen, Jarar, Nogob, Korahe, Shebele, and Dolo zones of the Somali Region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out Belg agricultural activities. On the other hand, the highest daily temperatures in Metema, Quara, Metekel, Gambella, Abobo, Fugendo, Lare, Gewane, Kebridehar and Gode will be recorded above 38-40 degrees Celsius.