Daily Weather Report 25 Mar 28

Weather Summary for previous day

March 27, 2025

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአዲግራት፣ ማይጨው፣ ወገልጤና፣ ኮምቦልቻ፣ መካነሰላም፣ አምባማሪያም፣ መሀልሜዳ፣ ሾላገበያ፣ ድሬዳዋ፣ ሐሮማያ፣ ጅግጅጋ፣ ጎብየሬ፣ ግራዋ፣ ኑራኤራ፣ ጨለንቆ፣ ገለምሶ፣ ሐረር፤ ሚኤሶ፣ አርሲ፣ ባሌሮቤ፣ ጊኒር፣ ጃራ፣ ያቤሎ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ፣ ቡሌሆራ ፣ ብላቴ ፣ ዲላ ፣ ቦሬ፣ ሐዋሳ፣ ባቱ ፣ቡኢ ፣ ቢሾፍቱ እና አቦምሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በሞያሌ እና በኩርፋጨሌ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተማ፣ ጋምቤላ፣ ቀብሪዳሃር እና ጎዴ ከ35.6-41.6 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday they had cloud cover over the Belg-benefiting areas of our country. In this regards, light to moderate amounts of rainfall were recorded in Adigrat, Maichew, Wegeltena, Combolcha, Mekansalam, Amba Mariam, Mehalmeda, Sholagebeya, Dire Dawa, Haramaya, Jigjig, Gobeyere, Grawa, Nuraera, Chelenko, Gemelso, Harar, Mieso, Arsi, Bale Robe, Ginner, Jara, Yabelo, Jinka, Konso, Bulehora, Bilate, Dilla, Bore, Hawassa, Batu, Bui, Bishoftu and Abomasa. In addition, heavy amounts of more than 30 mm rainfall were recorded in Moyale and Kurfachele. On the other hand the highest temperature of the day was recorded 35.6-41.6 degrees Celsius in Metema, Gambella, Kebridehar and Gode.

Weather Forecast for next day

March 29, 2025

በነገዉ ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅና ደቡብ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ጋቢና ሀሪ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን እና ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ፣ ሐረር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስከቶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ጌዲኦ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር እና ሸበሌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ዱብቲ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation over the Belg-benefiting areas of our country. In association with this, the central, east and south zones of Tigray region; from Amhara region east Gojjam, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone and north Shewa zones; from Afar region Gabi and Hari zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Kelem Wellega, west, southwest, north and east Shewa, east and west Hararge, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones of the Southwest Ethiopia region; from the central Ethiopia region Gurage, Hadia, Halaba, Silte, Yem special zone, Kembata and Tembaro; from Southern Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Amaro, Derashe, Burji, Konso, Gedeo and South Omo zones; all zones of Sidama region; from Gambella region Majang and Agnwuak zones; from the Somali region Fafen, Jarrar, Erer, Liben, Dawa, Afder and Shebelle zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm). On the other hand, the maximum temperature of the day will exceed 35 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Abobo, Lare, Fugnido, Dubti, Gewane, Awash Arba and Gode.