Daily Weather Report 25 Mar 27

Weather Summary for previous day

March 26, 2025

Yesterday, there was cloud coverage over the northeast, west, central, southwest and southern regions of our country. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Firewen, Miachew, Sirinka, Debre Work, Kombolcha, Bati, Wera Ilu, M/Meda, D/Birhan, Shola Gebeya, Addis Ababa, Waliso, Arsi Robe, Fiche, Bale Robe, Abomsa, Jigjiga, Harar, Gelemso, Kara Mille, Hirna, Kulubi, Gobeyere, Gode, Kebri Dar, Moyale, Yabelo, Bore, Tercha, Hawassa, and Sekoru. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 38 degrees Celsius in Gambella and Metema.

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በስንቃጣ፣ ማይጨዉ፣ ሲርንቃ፣ ደብረ ወርቅ፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲ፣ ጨፋ፣ ወረኢሉ፣ መሀል ሜዳ፣ ደብረ ብርሀን፣ ሾላ ገበያ፣ አዲስ አበባ፣ ወሊሶ፣ አርሲ ሮቤ፣ ፍቼ፣ ባሌ ሮቤ፣ አቦምሳ፣ ገለምሶ፣ ካራሚሌ፣ ሂርና፣ ቁሉቢ፣ ጎቢየሬ፣ ጂግጂጋ፣ ሐረር፣ ግራዋ፣ ጎዴ፣ ቀብሪዳር፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ቦሬ፣ ተርጫ፣ ወራቤ፣ ሐዋሳ እና ሶኮሩ ከቀላል እስከ መካከለኛ(1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝቷል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በፉኝዶ፣ ሰመራ እና አዋሽ አርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Weather Forecast for next day

March 28, 2025

በነገዉ ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመች የሆኑት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወክታቸው የሆኑት የደቡብ ምስራቅ ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ፣ ምስራቅ እና መካከለኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በተመሳሳዩ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል ደቡብ ምስራቀና ደቡብ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ወግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል ጋቢና ሀቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ፣ ሐረር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ፣ ሀላባ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ጋሞ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ጌዳሆ እና ደቡብ ኦሞ ዞንች፣ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል ማጃንግና አኙዋክ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል ሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ኢረር፣ ሊቤን እና አፍደር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሸካ፣ ከፋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ሸዋ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በዱብቲ፣ ሰመራ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ ቋራ እና ቀብረ ዳህር ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For tomorrow weather conditions conducive to rain will continue in the same manner in the Southeast, South, Southwest, Northeast, East, and Central regions of our country, which are the main and secondary rain sources of the autumn. In addition, from the Tigray region, the Southeastern and Southern zones; from the Amhara region, the Central, North and South Gondar, East Gojam, Wagmira, Oromo Nationality Special Zone, North Shewa, North and South Wollo zones; from the Afar region, the Gabi and Hati zones; from the Oromia region, the Jimma, East and West Hararge, Arsi and West Arsi, Bale and East Bale, Guji and West Guji, Borena and East Borena, North, West, Southwestern and East Shewa zones; Addis Ababa, Dire Dawa, Harar; from the Southwestern Ethiopia region, the Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; Central Ethiopia Region: Hadiya, Halaba, Silte, Zones; Southern Ethiopia Region: Wolaita, Gofa, Basketo, Gamo, Burji, Konso, Amaro, Derashe, Gedeo and South Omo Zones; All Sidama Region Zones; Gambella Region: Majeng and Agniwak Zones; Somali Region: Site, Fafen, Jarar, Erer, Liben and Afder Zones; Sheka, Kefa, East and West Hararge, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Bale and East Shewa will experience heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature will exceed 38 degrees Celsius in Dubti, Semera, Gambella, Abobo, Lare, Fugnido, Metema, Quara and Qebri Dahir.