Daily Weather Report 25 Mar 26

Weather Summary for previous day

March 25, 2025

በትናንትናው ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በስንቃጣ፣ አፅቢ፣ መቀሌ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ነፋስመዉጫ፣ ላሊበላ፣ ሲሪንቃ፣ ወገልጤና፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ መሀልመዳ፣ አለምከተማ፣ እነዋሪ፣ ደብረወርቅ፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላገበያ፣ ፍቼ፣ ካቺሴ፣ አምቦ፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ ጅማ፣ ጭራ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ፣ መተሀራ፣ አቦምሳ፣ ገለምሶ፣ ሚኤሶ፣ ኩርፋጨሌ፣ ሂርና፣ ካራሚሌ፣ ቁሉቢ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐሮማያ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ጃራ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ዶሎዶ፣ ቀብሪዳሃር፣ ሆሳዕና፣ ብላቴ፣ ወራቤ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ተርጫ፣ ማጂ፣ ጂንካ፣ ዲላ እና ቡርጂ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በመካነ ሰላም፣ ጊኒር እና ያቤሎ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በፉኚዶ፣ በአይሻ እና በቀብሪዳሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the areas of our country that benefited from the Belg rain season. As a result, in Senkata, Atsebi, Mekelle, Aider, Maichew, Nefasmewcha, Lalibela, Sirinka, Wegeltena, Kombolcha, Cheffa, Mehalmeda, Alemketema, Enewari, Debrework, Debremarkos, Yetnora, Debrebrehan, Sholagebeya, Fiche, Kachise, Ambo, Shambu, Nekemte, Jimma, Chira, Bishoftu, Adama, Metehara, Abomsa, Gelemso, Mieso, Kurfachele, Hirna, Karamile, Kulubi, Dire Dawa, Harar, Haromaya, Arsirobe, Balerobe, Jara, Bore, Negelle, Moyale, Dolodo, Kebridahar, Hosaina, Bilate, Werabe, Walaita Sodo, Tercha, Maji, Jinka, Dilla and Burji received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Moreover, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Mekane Selam, Ginir, and Yabelo. In contrast, the maximum daily temperature was recorded above 35°C in Gambella, Fugnido, Aisha, and Kebridahar.

Weather Forecast for next day

March 27, 2025

በነገው ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር፣ ዋግኽምራ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የፋንቲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ሸበሌ እና አፍዴር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ድሬዳዋ እና ስልጤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ገዋኔ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

For the upcoming day, widespread cloud coverage and accumulation are expected in areas of the country where Belg is the main and second rainy season. In relation to this, from Tigray region central, east, southeast and south zones; from Amhara region south Gondar, Waghemra, west Gojjam, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone and north Shewa Zones; from Afar region Fanti, Hari and Gabi zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, west, east, southwest and north Shewa, Arsi and west Arsi, east and west Hararge, Guji and west Guji, Bale and east Bale, Borena and east Borena zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Amaro, Derashe, Konso, Burji, south Omo and Gedeo zones; all zones of Sidama region; from Somali region Siti, Fafen, Jarar, Erer, Dawa, Liben, Shebelle and Afder will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Besides, Arsi and west Arsi, east and west Hararge, Bale, Dire Dawa, and Silte will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Conversely, in Humera, Metema, Quara, Metekel, Gambella, Lare, Abobo, Fugnido, Gewane, and Gode will record maximum daily temperature exceeding 38 degrees Celsius.