Daily Weather Report 25 Mar 21

Weather Summary for previous day

March 20, 2025

በትናንትናዉ ዕለት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በመቀሌ፣ አፅቢ፣ ፍረወይኒ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ላሊበላ፣ ንፋስ መውጫ፣ ወገል ጤና፣ ስሪንቃ፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ደብረ ወርቅ፣ መካነ ሰላም፣ ወረኢሉ፣ መሃል ሜዳ፣ አለም ከተማ፣ የትኖራ፣ ጉንዶ መስቀል፣ እንዋሪ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሾላ ገበያ፣ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ፍቼ፣ ካችስ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ሊሙ ገነት፣ ጅማ፣ ኩሉምሳ፣ አርሲ፣ ገለምሶ፣ ቦሬ፣ ባሌሮቤ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ቡሌሆራ፣ ሐሮማያ፣ ሐዋሳ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ሰኮሩ፣ ተርጫ፣ አርባምንጭ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ብላቴ፣ ግራዋ እና ሐረር ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በአዲግራት፣ ጭራ፣ ወላይታ ሶዶ እና ዲላ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል ፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተማ፣ መተሐራ እና ጎዴ ከ37-41 ዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday there was a strong cloud cover in the areas of our country that benefited from the autumn rains. In connection with this, Mekelle, Atsbi, Freweini, Aider, Maychew, Lalibela, Nefas Mewicha, Wogel Tena, Srinka, Combolcha, Chefa, Debre Work, Mekane Selam, Wereilu, Mehal Meda, Alem Ketema, Yetenora, Gundo Meskel, Enwari, Debre Birhan, Light rainfall was recorded in Shola Market, Addis Ababa, Adama, Fiche, Kachis, Ambo, Woliso, Limu Genet, Jimma, Kulumsa, Arsi, Gelemso, Bore, Balerobe, Negele, Moyale, Bulehora, Haromaya, Hawassa, Emdiber, Hosanna, Warabe, Sekoru, Tercha, Arbaminch, Saula, Jinka, Burji, Konso, Bilate, Girawa and Harar. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Adigrat, Chira, Wolaita Sodo and Dilla. On the other hand, the highest temperatures of the day were recorded in Metema, Methara, and Gode, ranging from 37-41 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

March 22, 2025

በነገዉ ዕለት በልግ ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ዝናብ ሰጪ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ይበልጥ እንደሚጠናከሩና እንደሚስፋፉ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ፣ አዉሲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ሆሩጉድሩ፣ ቄለምና ምስራቅ ወለጋ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን ፣ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ ዞኖች፣ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ አፍዴር እና ኤረር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ፣ ጅማ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ሸካ፣ ከፋ እና ስልጤ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በቀብሪደሃር፣ ላሬ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ሁመራ ፣ መተከል፣ መተማ እና ቋራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38-42 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

Tomorrow Forecast data indicates that the main and second rainy seasons of the Belg will intensify and spread further in the areas of our country.. In addition, the Northwestern, Central, Eastern, Southeastern and Southern zones of Tigray Region; the Central, North and South Gondar, North and South Wollo, Waghimra, Oromo Nationality Special Zone, West and East Gojam and North Shewa Zones of Amhara Region; the Kelbeti, Fanti, Hari, Awsi and Gabi Zones of Afar Region; the Jimma, Buno Bedele, Buno Bedele, Ilubabor, West, East, Southwest and North Shewa, East and West Hararge, Horugudru, Kelem and East Wellega, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Borena and East Borena zones; Addis Ababa, Dire Dawa, Harar; Itang, Nuer, Agnuk and Majang zones from Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem liyu Zone, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region, The Wolaita, Gofa, Basketo, South Omo, Amaro, Derashe, Konso and Burji zones of the Southern Ethiopian Region, all zones of the Sidama Region, and the Siti, Afder and Erer zones of the Somali Region will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, North and South Wollo, North Shewa, Oromo Nationality Special Zone, Kelbeti, Fanti, Gabi, Jimma, East Shewa, Sheka, Kefa and Silte will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the highest daily temperatures in Kebridehar, Lare, Gambella, Abobo, Fugendo, Humera, Metekel, Metema and Quara will be recorded above 38-42 degrees Celsius.