Daily Weather Report 25 Mar 20
Weather Summary for previous day
Yesterday, there was cloud cover overage over the northeast, west, central, southwest and southern regions of our country. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Mekelle, Lalibela, Nefas Mewucha, Sirinka, Mekane Selam, Kombolcha, Enwari, Debre Berhan, Mehal Meda, Gewane, Gambella, Tepe, Aman, Maji, Hosanna, Moyale, Negele, Konso, Bule Hora, Dolo Odo, Kachise, Addis Ababa, Fiche, Kulumsa, Mieso, Arsi Robe, Dolo Mena, Bale Robe, Haromaya, Harar, Hawassa and Kurfa chele, Chelenko, Girawa and Qulbi. In addition, heavy rainfall was recorded in Bore and Jigjiga. On the other hand, the highest daily temperature was recorded above 38 degrees Celsius in Gambella, Lare, Fugnido, Gode, Semera, Pawe and Metema.
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በመቀሌ፣ በላሊበላ፣ በንፋስ መዉጫ፣ በሲርንቃ፣ መካነ ሰላም፣ ኮምቦልቻ፣ ኢንዋር፣ ደብረ ብርሃን፣ መሀል ሜዳ፣ ገዋኔ፣ ጋምቤላ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ማጂ፣ ሆሳዕና፣ ሞያሌ፣ ነግሌ፣ ኮንሶ፣ ቡለ ሆራ፣ ዶሎ ኦዶ፣ ካችስ፣ አዲስ አበባ፣ ፍቼ፣ ቦሬ፣ ጂግጂጋ፣ ኩሉምሳ፣ ሚሄሶ፣ አርሲ ሮቤ፣ ዶሎ መና፣ ባሌ ሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ሀረር እና ሀዋሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ(1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙት ሲሆን በቦሬና ጂግጂጋ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፣ ፡፡በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በላሬ፣ በፉኝዶ፣ በጎዴ፣ በሰሜራ፣ በፓዌ እና በመተማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Weather Forecast for next day
For Tomorrow weather conditions favourable for rain formation will continue to intensify in the Southeast, South, Northeast, Southwest, Central, and Eastern regions of our country, which benefit from the belg rains. In this regard, the Central, East, Southeast and South Zones of Tigray Region; North and South Gondar, North and South Wello, Waghimira, Oromo Nationality Special Zone, East Gojam and North Shewa Zones of Amhara Region; Kelbeti, Fanti, Hari, Awsi and Gabi Zones of Afar Region; Jimma, Buno Bedele, Ilu Babor, East and West Hararge, Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Borena and East Borena Zones of Oromia Region; Addis Ababa, Dire Dawa, Harar; Itang, Agnuak and Majeng zones of Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of Southwestern Ethiopia region; Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special Zone, Kembata and Tanbaro zones of Central Ethiopia region; Wolaita, Gofa, Basketo, South Homo, Amaro, Derashe, Konso and Burji zones of Southern Ethiopia region; all Sidama region zones; Liben and Afder zones of Somali region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, Bench Sheko, Sheka, Kefa, Kelbeti, Fanti, Gabi, North and South Wello, North Shewa, Oromo Nationality Special Zone, Gurage, Silte, Guji and West Guji will receive heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will be above 38 degrees Celsius in Kebre Dahir, Lare, Gambella, Abobo, Fugnido, Humera, Metekel, Metema and Quara.
በነገዉ ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ለበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል ማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፣ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኽምራ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፣ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ፣ አዉሲ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ ባቦር፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፣ ድሬ ዳዋ፣ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ አኙዋክና ማጀንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን ፣ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ደቡብ ሆሞ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ እና ቡርጂ ዞንች፣ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል ሊቤንና አፍደር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በቀብረ ዳህር፣ ላሬ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፣ ሁመራ ፣ መተከል፣ መተማ እና ቋራ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡