Daily Weather Report 25 Mar 19

Weather Summary for previous day

March 18, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ ፍረወይኒ፣ አፅቢ፣ ላሊበላ፣ ነፋስ መውጫ፣ ሲሪንቃ፣ ወገል ጤና፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ መሀልሜዳ፣ መካነሰላም፣ የትኖራ፣ ደብረብርሀን፣ አዲስ አበባ፣ ፍቼ፣ ካቺስ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ፣ ኢጃጂ፣ አምቦ፣ አዳማ፣ ባሌሮቤ፣ ዶሎመና፣ ነገሌ፣ ቡሌሆራ፣ ያቤሎ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ምዕራብ አባያ፣ ዲላ፣ ኮንሶ፣ ሐዋሳ፣ ሆሳዕና፣ እምድብር፣ ወራቤ፣ ሒርና፣ ግራዋ፣ ኩርፋጨሌ እና ጅግጅጋ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ፣ ባቲ፣ ገለምሶ፣ ቡኢ፣ ማጂ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ በሰመራ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ በጋምቤላ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was a strong cloud cover over the northeastern, central, eastern and southern regions of our country. In connection with this, there were thunderstorms in Mekelle, Freweini, Atsbi, Lalibela, Neifas Mewicha, Srinka, Wogel Tena, Combolcha, Chefa, Mehalmeda, Mekan selam, Yetnora, Debre Birhan, Addis Ababa, Fiche, Kachis, Bishoftu, Jimma, Ejaji, Ambo, Adama, Balerobe, Dolo mena, Negele, Bulehora, Yabelo, Aman, Tercha, Wolaita Sodo, Saula, Jinka, West Abaya, Dilla, Konso, Hawasa, Hosanna, Emdiber, Warabe, Hirna, Girawa, Kurfachele and Jigjiga received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Addis Ababa, Bati, Gelemso, Bui, Maji. On the other hand, the highest daily temperature was recorded above 38°C in Metema, Samara, Gewane, Awash Arba, Gambella and Gode.

Weather Forecast for next day

March 20, 2025

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በደቡብ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ይበልጥ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ማሂ፣ አዉሲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖበደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ እና ሸበሌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡በተጨማሪም ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ፤ጋቢ እና አውሲ ዞኖች በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ገዋኔ፣ ዳልፋጊ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, weather events favorable for rainfall formation will intensify in the Belg-benefiting areas of the southern, southeastern, southwestern, northeastern, central and eastern parts of our country. In association with this, from Tigray region central, eastern, southeastern and southern zones; from Amhara region north and south Wollo, Oromo Ethnic Special zone, Waghemra, north Shewa, east Gojjam, north and south Gondar zones; from Afar region Kilbetti, Mahi, Awsi, Fanti, Hari and Gabi zones; from Oromia region Jimma, Bunobedele, Kelem Wellega, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, west and east Hararge, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones; Addis Ababa, Harar, Dire Dawa; From the Benishangul Gumuz region, Asosa and Maokomo zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from Gambella region: Agnuwak, Majang and Itang zones; from central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; Sidama regional zones; Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Alle, Derashe, Amaro, Burj, Konso, South Omo and Gedeo zones and from Somali region Siti, Fafen, Jarrar, Erer, Dawa, Liben, Afder, Korahe and Shebelle zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm). Additionally, North and South Wollo, Oromo Nationality Special Zone, and North Shewa; Gabi and Awsi zones of Amhara Region will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, numerical forecast information indicates that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Pawe, Gambella, Lare, Fugnido, Gewane, Awash Arba and Gode.