Daily Weather Report 25 Mar 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አፅቢ፣ ስንቃጣ፣ አዲግራት፣ ማይጨው፣ ላሊበላ፣ ሲሪንቃ፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ወረኢሉ፣ ማጀቴ፣ መሀልሜዳ፣ መካነሰላም፣ ደብረወርቅ፣ እንዋሪ፣ ደብረብርሀን፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐሮማያ፣ ቢሾፍቱ፣ ጅማ፣ አርሲሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ጃራ፣ ቦሬ፣ ነገሌ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ እንድብር፣ ብላቴ፣ ወላይታሶዶ፣ ዲላ፣ ጅንካ እና ጅግጅጋ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በቡሌሆራ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፓዌ፣ በአይሻ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the northeast, central, east, southwest and southern parts of Our Country. In this regard, Atsibi, Senkata, Adigrat, Maichew, Lalibela, Sirinka, Combolcha, Cheffa, Wereilu, Majete, Mehalmeda, Mekansalam, Debre work, Enwari, Debre Birhane, Addis Ababa, Dire Dawa, Haramaya, Bishoftu, Jimma, Arsi Robe, Bale Robe, Jara, Bore, Negele, Moyale, Yabelo, Emdibir, Bilatte, Wolaitasodo, Dilla, Jinka and Jigjig received light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall, and also more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Bulehora. On the other hand, in Pawe, In Aisha and Gode, the maximum temperature of the day was recorded as above 35°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት በደቡብ፣ በደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ አዉሲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖበደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ቆራሄ፣ ሸበሌ እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, weather events favorable for rainfall formation will intensify in the Belg-benefiting areas of the southern, southeastern, southwestern, northeastern, central and eastern parts of our country. In association with this, from Tigray region central, eastern, southeastern and southern zones; from Amhara region north and south Wollo, Oromo Ethnic Special zone, Waghemra, north Shewa, east Gojjam, north and south Gondar zones; from Afar region Kilbetti, Awsi, Fanti, Hari and Gabi zones; from Oromia region Jimma, Bunobedele, Kelem Wellega, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, west and east Hararge, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones; Addis Ababa, Harar, Dire Dawa; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dauro zones; from Gambella region: Agnuwak, Majang and Itang zones; from central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata and Tembaro zones; Sidama regional zones; Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Alle, Derashe, Amaro, Burj, Konso, South Omo and Gedeo zones and from Somali region Siti, Fafen, Jarrar, Erer, Dawa, Liben, Afder, Korahe, Shebelle and Doolo zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm). On the other hand, numerical forecast information indicates that the maximum temperature of the day will exceed 38 degrees Celsius in Humera, Metema, Quara, Metekel, Pawe, Gambella, Lare, Fugnido, Gewane, Awash Arba and Gode.