Daily Weather Report 25 Mar 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የምስራቅ ትግራይ ዞን፤ የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የአዉሲ ዞን፤ የአርሲ፣ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ በአዋሽ አርባ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the northeastern, central, southern, and eastern areas of the country. In this regard, in the eastern Tigray zone; eastern Gojjam, north Shewa, north and south Wollo zones; Awusi zone; Arsi, Bale, Borena and east Shewa zones; Addis Ababa; Walaita, Gamo, Gofa, Konso, Burji, south Omo and Gedeo zones and Sidama region zones light to moderate rainfall was recorded In contrast, the maximum temperature of the day was recorded exceeding 38°C in Fugnido, Gambella, Awash Arba and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፣ ምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ማጃንግ እና ኢታንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኤሬር፣ ጃራር፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ መተከል፣ ላሬ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ገዋኔ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
For the upcoming day, the weather conditions favorable for the formation of Belg rains will continue to strengthen over the northeast, southwest, south, central, southeast, and east portions of the country. Consequently, from Tigray region the south, southeast and east zones; from Amhara region east Gojjam, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, Waghemra and north Shewa zones; from Afar region Awusi, Fanti, Hari and Gabi zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam Wellega, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and east Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones, east and west Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from the central Ethiopian region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Kefa, Sheka, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the south Ethiopian region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Konso, Burji, Amaro, south Omo and Gedeo zones; from Gambella region Agnuak, Majang and Itang zones; Sidama region zones and from Somali region Siti, Fafen, Erer, Jarar, Dawa, Liben, Korahe and Doollo zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Conversely, numerical weather forecast information shows that the maximum temperature of the day will exceed 38°C in Humera, Metema, Metekel, Lare, Abobo, Gambella, Fugnido, Gewane and Gode.