Daily Weather Report 25 Mar 16
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በደባርቅ፣ ጭራ፣ ሳውላ እና ማጂ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተሐራ 38.1፣ በጋምቤላ 38.8 እና በጎዴ 40.4፣ በዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the northeast, northwest, west, central, south and southwest regions of our country. In connection with this, light rain was recorded in Debark, Chira, Sawla and Maji. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded at 38.1 degrees Celsius in Methara, 38.8 in Gambella and 40.4 in Gode.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ዋግኽምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ፣ ፋንቲ፣ ሀሪ፣ጋቢ እና ሀቲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ምዕራብ፣ ቄለም፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ደራሼ፣ ጌዳኦ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌርና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ሐረር እና ድሬዳዋ፤ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር እና ዶሎ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions favorable for the occurrence of Belg rains will have a better appearance in the northwest, northeast, central, east, southwest and southern regions of our country. In this regard, the southeast, east and south zones of Tigray region; North and south Wollo, central, north and south Gondar, Oromo Nationality Special Zone, east and west Gojam, Waghimra and north Shewa zones of Amhara region; From the Afar region, the zones of Awsi, Fanti, Hari, Gabi and Hati; Addis Ababa; from the Oromia region, the zones of Jimma, Ilubabor, Bunobdele, West, Kelem, East and Horogudru, Wellega, West, South West, North and East Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji, Borena and East Borena, East and West Hararge zones; from the Central Ethiopia region, Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Zone, Kembata and Tembaro zones; From the Southwestern Ethiopian Region: Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; from the Southern Ethiopian Region: Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Gedeo, Burji, South Omo and Konso zones; from the Gambella Region: Agnewak, Nuer and Majang zones; from the Sidama Region: all zones; Harar and Dire Dawa; from the Benshangul Gumuz Region: Asosa, Kamash and Maokomo zones; In the Somali region, the Siti, Dawa, Liben, Afder and Dolo zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) at many places. On the other hand, the daily maximum temperature in Metema, Metekal, Pawe, Abobo, Gambella, Lare, Fugendo, Kebridehar and Gode is expected to exceed 38 degrees Celsius.