Daily Weather Report 25 Mar 15

Weather Summary for previous day

March 14, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በአምባ ማርያም እና ማጂ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተሐራ 38.5፣ በጎዴ 40.6፣ በጋምቤላ 42.2 እና በፉኝዶ 42.5 በዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in the northeast, northwest, west, central, south and southwest regions of our country. In connection with this, light rain was recorded in Amba Mariam and Maji. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded at 38.5 degrees Celsius in Methara, 40.6 in Gode, 42.2 in Gambella and 42.5 in Fugendo.

Weather Forecast for next day

March 16, 2025

በነገዉ ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ዋግኽምራ እናሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአዉሲ፣ ሀሪ፣ጋቢ እና ሀቲ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ደራሼ፣ ጌዳኦ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ሐረር እና ድሬዳዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions favorable for the occurrence of Belg rains will continue to strengthen in the northwest, northeast, central, east, southwest and southern regions of our country. In connection with this, the North and South Wollo, Central, North and South Gondar, Oromo Nationality Special Zone, East and West Gojam, Waghimra and North Shewa zones of the Amhara region; the Awsi, Hari, Gabi and Hati zones of the Afar region; Addis Ababa; From the Oromia Region, Jimma, Ilubabor, Bunobdele, East and Horogudru, Wellega, West, South West, North and East Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, Guji and West Guji, Borena and East Borena zones, East and West Hararge zones; from the Central Ethiopia Region, Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Zone, Kembata and Tembaro zones; Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro zones of Southwestern Ethiopia; Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Gedeo, Burji, South Omo and Konso zones of Southern Ethiopia; Agnewak and Majang zones of Gambella region; all zones of Sidama region; Harar and Dire Dawa will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature will exceed 38 degrees Celsius in Metema, Metekel, Pawe, Abobo, Gambella, Lare, Fugendo, Kebridehar, and Gode.