Daily Weather Report 25 Mar 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በመካነ ሰላም፣ ሻምቡ፣ ኢጃጂ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ጭራ፣ ሊሙ ገነት፣ ጅማ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ ጅንካ፣ አማን፣ አምቦ፣ የትኖራ፣ ዲላ ፣ አንገርጉትን፣ ምዕራብ አባያ፣ ቴፒ፣ ሰኮሩ፣ ኮምቦልቻ፣ ጨፋ፣ ደብረ ወርቅ፣ አምደ ወርቅ፣ ደባርቅ፣ ፍረወይኒ፣ በዓዲግራት እና በዓድዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ(1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመተማ 38.0 እና በፉኝዶ 39.5 በዲግሪ ሴልሺየስ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the northeast, northwest, west, central, southern and southwest parts of our country. In line with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Mekane Selam, Shambu, Ijaji, Nekemte, Arjo, Bedele, Cira, Limmu Genet, Jimma, Masha, Tercha, Jinka, Aman, Ambo, Yitinora, Dilla, Angergutina, MirabAbaya, Tepi, Sokoru, Combolcha, Cheffa, Debrework, Amba Mariam, Debark, Freweyni, Adwa and Adigrat. On the other hand, the maximum temperature of the day in Metema 38 and Fugnedo 39.5 degrees Celsius was recorded.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ገጽታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉባቦር እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ አዋሽ አርባ፣ ሚሌ፣ ኤሊዳር ፣ ገዋኔ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, Weather events favorable for the formation of Belg rain will have a better way over the northwest, west, central, southern and southwest parts of Our Country. from Amhara region Central, West, North and South Gondar south, Awi zone, North and South Wollo, Waghemra, East and West Gojjam Zones; from Oromia region Jimma, Buno Bedele Ilubabor and Horo Guduru Welega zones; from the Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, and West Omo Zones will receive light to moderate amounts of rainfall. On the other hand, in Gambella, Abobo, Lare, Fugnedo, Metema, Quara, Metekel, Pawe, Dubti, Semera, Awash Arba, Mille, Elidar, Gewane, Kebridahar and Gode will have the highest temperature for the day to exceed 38°C.