Daily Weather Report 25 Mar 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያይዘም በላሊበላ፣ መተከል፣ መካነ ሰላም፣ ካችስ፣ ሻምቡ፣ ኢጃጂ፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ሊሙ ገነት፣ ጅማ፣ ጎሬ፣ ማሻ፣ ተርጫ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ሀዋሳ፣ ጂንካ፣ ሳዉላ እና አማን ከቀላል እስከ መካከለኛ(1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝቷል፡፡በሌላ በኩል በጋምቤላ እና በመተማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud coverage over the northeast, west, central, southwest and southern regions of our country. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Lalibela, Metekel, Mekane Selam, Kachis, Shambu, Ijaji, Nekemte, Arjo, Bedele, Gatira, Cira, Limmu Genet, Jimma, Gore, Masha, Tercha, Emdibir, Hosaina, Hawassa, Jinka, Saula and Aman. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 38 degrees Celsius in Gambella and Metema.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል ምዕራብ ዞን፣ ከአማራ ክልል የማዕከላዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ እና ደቡብ ኦሞ ዞንች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ከፋ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በዱብቲ፣ ሰመራ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ መተማ፣ ቋራ እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For tomorrow Weather conditions favourable for the occurrence of Belg rains will continue to be strong in the north, northwest, west, central, southwest and south of our country. In this regard, From the Tigray region western zone; From the Amhara region central, western, north and south Gondar, Awi zone, east and west Gojam zones; From the Benishangul Gumuz region Metekel zone; From Oromia region Jimma, Buno Bedele, East and Horo Guduru Welega zones; From the Southwestern Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones; and from the South Ethiopia region Wolaita, Gofa, Basketo and South Omo zones will expected light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Bench Sheko, Sheka and Kefa will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum daily temperature will exceed 38 degrees Celsius in Dubti, Semera, Gambella, Abobo, Lare, Fugnido, Metema, Quara, and Gode.