Daily Weather Report 25 Mar 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በመካከለኛው፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ደብረማርቆስ፣ መካነሰላም፣ የትኖራ፣ ጉንዶመስቀል፣ አለም ከተማ፣ ሻምቡ፣ ነቀምቴ፣ ካችስ፣ ኢጃጅ፣ ሊሙገነት፣ በደሌ፣ ጅማ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ሆሳዕና፣ ሀዋሳ፣ ብላቴ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ተርጫ፣ አማን እና ቴፒ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ እና በጋምቤላ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the central, southwestern and southern regions of our country. In this regard, Debre Markos, Mekaneslam, Yetnora, Gundomeskel, Alem Ketema, Shambu, Nekemte, Kachis, Ejaj, Limugenet, Bedele, Jimma, Gatira, Chira, Hosana, Hawasa, Bilate, Wolaytasodo, Saula, Jinka, Tercha, Aman and Tepi received light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, the highest daily temperature in Metema and Gambella was recorded above 38°C.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክና ማጃንግ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ቀብሪደሃር እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, Meteorological features favorable for the formation of Belg rains will continue over the northwest, northeast, west, central, eastern, southwest and southern parts our country. In association with this, the central, northwest, southeast, east and south zones of the Tigray region; from Amhara region north and south Wollo, Waghemra, north, central and south Gondar, east and west Gojjam zones; from Oromia region Jimma, Illubabor Bunobedele, east and Horogudru Wellega, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones; from the Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Gambella region Agnewak and Majang zone; Sidama region zones; From the Southern Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Amaro, Burj, Konso, South Omo and Gedeo zones receive light to moderate amounts of rainfall. On the other hand, the maximum temperature for the day will exceed 38 degrees Celsius in Metema, Metekel, Pawe, Abobo, Gambella, Lare, Fugnido, Kebridehar and Gode.