Daily Weather Report 25 Mar 11

Weather Summary for previous day

March 10, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ነፋስመውጫ፣ ላሊበላ፣ ሲሪንቃ፣ ወረኢሉ፣ መካነሰላም፣ ደብረማርቆስ፣ የትኖራ፣ ጉንዶመስቀል፣ አዋሽ አርባ፣ ካችስ፣ ኢጃጅ፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ ወሊሶ፣ ኩልምሳ፣ ባሌሮቤ፣ ቦሬ፣ ቡሌሆራ፣ ሞያሌ፣ እንድብር፣ ወራቤ፣ ቡኢ፣ ሀዋሳ፣ ብላቴ፣ ወላይታሶዶ፣ ምዕራብ አባያ፣ አርባምንጭ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ኮንሶ፣ ዲላ፣ ተርጫ፣ ሐሮማያ እና ድሬዳዋ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሆሳዕና እና በቡርጅ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ በጋምቤላ እና በገዋኔ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the northeast, central, eastern, southwest and southern parts of our country. In this regard, Nefasmewicha, Lalibela, Sirinka, Wereilu, Mekaneselam, Debre Markos, Yetnora, Gundomeskel, Awash Arba, Kachise, Ejaji, Limugenet, Jimma, Sokoru, Woliso, Kulumsa, Bale Robe, Bore, Bulehora, Moyale, Emdibir, Werabe, Bui, Hawassa, Bilate, Wolaitasodo, Mirab Abaya, Arba Minch, Sawla, Jinka, Konso, Dilla, Tercha, Haramaya and Dire Dawa received light to moderate (1-29 mm) amounts of rain. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm rain was recorded in Hosanna and Burj. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 38°C in Metema, Gambella and Gewane.

Weather Forecast for next day

March 12, 2025

በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የሚቲዎሮሎጂ ገፅታዎች በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ቡኖበደሌ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ እና ጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, Meteorological features favorable for the formation of monsoon rains will continue over the northwest, northeast, west, central, eastern, southwest and southern parts our country. In association with this, the central, northwest, southeast, east and south zones of the Tigray region; from Amhara region north and south Wollo, Waghemra, north, central and south Gondar, east and west Gojjam zones; from Oromia region Jimma, Bunobedele, east Wellega, Horogudru Wellega, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale, west and east Hararge, Guji and west Guji, Borena and east Borena zones; Addis Ababa, Harar, Dire Dawa; from the Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; from Gambella region Agnewak zone; from central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special zone, Kembata and Tembaro; Sidama region zones; From the Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Baskete, Derashe, Amaro, Burj, Konso, South Omo and Gedeo zones and from Somali region Fafen zone receive light to moderate amounts of rainfall. On the other hand, the maximum temperature for the day will exceed 38 degrees Celsius in Metema, Quara, Metekel, Pawe, Gambella, Lare, Fugnido, Gewane, Awash Arba and Gode.