Daily Weather Report 25 Mar 09

Weather Summary for previous day

March 8, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በለሌበላ፣በደብራ መርቆስ፣ በመከና ሰለም፣ በአርጆ፣ በጂማ፣ በአዋሳ፣በጂንካ፣ በሳዉላ፣ በሞያሌ፣ በአርባ ምንጭ፣ በወለይታ እና በነገሌ ከቀላል እስከ ከመከካለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ጋምቤላ፣በቢላቴ እና በመተሀራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the northeast, central, western, southwestern and southern regions of our country. In this regard, light to heavy rainfall was recorded in Lallibala, Debra Markos, Mekaneselam, Arjo, Jima, Sawula, Moyale,Neghele, Hawasa, Wolayita, and Arba Minch. On the other hand, the Maximum temperature of the day was recorded above 35°C in, Gambella, Bilate Assosa and Metehara.

Weather Forecast for next day

March 10, 2025

በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሀኔታ ክስተቶች በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፤በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ በሆኑት አከባቢዎች ላይ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ፋንቲ፣ አዉሲ እና ሀቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋ(ሰላሌ)፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና፣አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ባሌና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ሸጋር ከታሞች፣ ዲሬ ዳዋ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ደራሼ፣ኮንሶ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች እና በሶማሊ ከልል ሲቲ ዞን፣ ፈፋን፣ ኤሬር፣ሊበን እና ሸበሌ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ፣ፋንቲ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ቦረናእና ምስራቅ ቦረና 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ እና በመታማ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For the next day, weather events favorable to the formation of Belg rainfall will continue to enhance rains will continue over north, north east, central, south and south west in the areas of our country. In line with this, the central, northeast, south,eastern, southern, southwestern and eastern zones of the Tigray region; from the Amhara region west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra Zones; from the Afar region Kilbeti, Gabi, Fanti, Awusi and Hari zones;; from the Oromia region Jimma, southwest Shewa, east Shewa, north Shewa(Salale) and west Shewa,; Addis Ababa; Shagar Cities, from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Halaba, Hadiya, Yem special zone, Kambata and Tembaro Zones; from south Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Dareshe, and Basketo zones; all zones of Sidama region and Siti zone ,Afdar, Erer and Shabele of Somali region will receive light to moderate rainfall in many places. In addition, east and south Tigray, north and south Walo, Oromo special zone, Fanti, Borena ans east Borena east and west Hararge will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out Belg agricultural activities. On the other hand, the numerical forecast information indicates that the maximum temperature of the day will be above 38 degrees Celsius in Gambella, Lare, Fugnido, Abobo, Awash Arba, Gode and Kebridahar.