Daily Weather Report 25 Mar 07

Weather Summary for previous day

March 6, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በላሊበላ፣ ጋቲራ፣ ማሻ፣ደብር ወርቅ፣ነፋስ መውጫ፣ጭራ፣ጅማ እና በወገል ጠና ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በላሬ፣ ፓዌ፣ጋምቤላ፣ገዋኔ ፣ አዋሽ አርባ እና በመተሀራ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the northeast, central, western, southwestern and southern regions of our country. In this regard, light to moderate rainfall was recorded in Lalibela, Gatira, Masha, Debar Work, Nefas Mewcha, Cira, Jimma and Wegeltena. On the other hand, the Maximum temperature of the day was recorded above 38°C in Lare, Pawe, Gambella, Gewane, Awash Arba and Metehara.

Weather Forecast for next day

March 8, 2025

በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፤በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር፣ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ አውሲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ፣ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ በሐረር፤ በደሬዳዋ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ እና ምስራቅ ጉራጌ ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ ደራሸ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በመሆኑም የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ አቦቦ፣ ሰመራ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና በቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, our Weather forecast information indicates that weather conditions favourable for the occurrence of Belg rains will intensify in the North-East, west, and Central, East, South, South-West and Southeast areas of our country. In this regard, the Central, East, Southeast and South Zones of Tigray Region; South Gondar, East Gojam, Waghemra, Oromo Nationality Special Zone, North and South Wollo and North Shewa Zones of Amhara Region; Kilbeti, Fanti, Awsi, Gabi and Hari Zones of Afar Region; Jimma, West, Southwest, North and East Shewa, West and East Hararge, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, Borena and East Borena Zones of Oromia Region; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; The zones of Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawuro in the Southwestern Ethiopia region; the zones of Gurage and East Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem special Zone, Kembata and Tembaro in the Central Ethiopia region; the zones of Sidama Region and the zones of Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, Ale, Derashe, Burji, Amaro, South Omo, Konso and Gedeo in the Southern Ethiopia region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Therefore, the amount and distribution of rainfall will be of great importance for carrying out Belg agricultural activities. On the other hand, the numerical forecast information indicates that the maximum temperature of the day will be above 38 degrees Celsius in Gambella, Lare, Fugnido, Abobo, Semera, Awash Arba, Gode and Kebridahar.