Daily Weather Report 25 Mar 06

Weather Summary for previous day

March 5, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ላሊበላ፣ ሲሪንቃ፣ ኮምቦልቻ፣ ወረኢሉ፣ መሀልሜዳ፣ የትኖራ፣ እንዋሪ፣ ፍቼ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ ጎሬ፣ ሊሙገነት፣ ጋቲራ፣ ሆሳዕና፣ ሀዋሳ፣ ማሻ፣ ተርጫ እና ቴፒ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ በጋምቤላ፣ በአቦቦ፣ በመተሀራ፣ በገዋኔ እና በአዋሽ አርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the northeast, central, west, southwest and southern parts of our country. In line with this, Lalibela, Sirinka, Combolcha, Wereilu, Mehalmeda, Yitnora, Enwari, Fiche, Angergutn, Nekemte, Gore, Limugenet, Gatira, Hosanna, Hawassa, Masha, Tercha and Tepi received light to moderate (1-29 mm) amounts of rain. On the other hand, the maximum daily temperature was recorded above 38°C in Metema, Gambella, Abobo, Metehara, Gewane and Awash Ariba.

Weather Forecast for next day

March 7, 2025

በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ ገፅታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም እና ሰሜን ሸዋ፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ የሲዳማ ክልል እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ እና ጌዲኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ገዋኔ፣ አዋሽ አርባ፣ ጎዴ እና በቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, Weather events favorable for the formation of Belg rain will have a better way over the northwest, northeast, central, east, southwest and southern parts of Our Country. from Amhara region south Wollo, Oromo Ethnic Special Zone, Waghemra, North and South Gondar, East Gojjam and North Shewa from the Afar Region, Fanti, Aussie and Hari Zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and West Arsi, Bale, East Hararge, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; from the Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Fafa, Konta, West Omo and Dauro; Majang Zone from Gambella region; Central Ethiopia region: Gurage, Silte, Hadia, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro; Sidama Region and Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe and Gedeo zones receive light to moderate amounts of rainfall. On the other hand, in Metema, Quara, Metekel, Pawe, Gambella, Lare, Fugnedo, Gewane, Awash Arba, Gode and Kebridehar will have the highest temperature for the day to exceed 38°C.