Daily Weather Report 25 Mar 05

Weather Summary for previous day

March 4, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ማይጨው፣ ጽጽቃ፣ ወገል ጤና፣ ወረኢሉ፣ ጉንዶ መስቀል፣ እንዋሪ፣ ፍቼ፣ ኢጃጂ፣ ወሊሶ፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ ኩሉምሳ፣ ማሻ፣ አማን፣ ሰኮሩ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና ወራቤ እና ሐዋሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በላሬ፣በፉኝዶ፣ በጋምቤላ፣ በገዋኔ እና በአዋሽ አርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover in the North-East, Central, West and South-West areas of our country. In relation to this, Maichiwu, Tsitsaka, Wogel Tena, Wereilu, Gundo Mesekel, Enwari, Fiche, Ejaji, Woliso, Limugenet, Jimma, Kulumsa, Masha, Aman, Sekoru, Emdiber, Hosaina Warabe and Hawasa received light to moderate (1-29 mm) rain. On the other hand, in Lare, Funedo, Gambella, Gewane and Awash Arba, the maximum temperature of the day was recorded as more than 38°C.

Weather Forecast for next day

March 6, 2025

በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግኸምራ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ጉጂ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ እና ጌዲኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ስለሆነም በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የሚስተዋለው የዝናብ መጠንና ስርጭት የበልግ ግብርና እንቅስቃሴ ለማከናወን ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ እና ገዋኔ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions favorable for the formation of Belg rains will continue to strengthen in the North-West, North-East, Central, South-West and South areas of our country. Along with this, the southeast, east and south zones of the Tigray region; North and South Wolo, North Shewa, Waghemra and East Gojam zones from Amhara region; From Oromia Region, Jimma, Ilubabor, West, South West, North and East Showa, Arsi and West Arsi, Bale and Guji zones; In Addis Ababa. Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta and Dawuro zones from South West Ethiopia region; From Gurage, Silte, Hadiya, M Special Zone, Kembata and Tembaro Zones of Central Ethiopia Region; Zones of Sidama region and Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe and Gedo zones of Southern Ethiopia will receive light to moderate rainfall. Therefore, the amount and distribution of rainfall observed in different areas of our country creates a favorable environment for carrying out Belg agricultural activities. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will be above 38°C in Metema, Quara, Mekele, Pawe, Gambella, Abobo, Lare, and Gewane.