Daily Weather Report 25 Mar 04
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ማይጨው፣ ጽጽቃ፣ ላሊበላ፣ ሞጣ፣ የትኖራ፣ እንዋሪ፣ ፍቼ፣ አርጆ፣ አልጌ፣ ጎሬ፣ በደሌ፣ ሊሙገነት፣ ጋቲራ፣ ማሻ እና አማን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ በጋምቤላ፣ በገዋኔ እና በአዋሽ አርባ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had cloud cover in the northeast, central, west and southwestern parts of our country. In this regard, Maichiwu, Tsitsaka, Lalibala, Mota, Yetnora, Enwari, Fiche, Arjo, Alge, Gore, Bedele, Limugenet, Gatira, Masha and Aman received light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall. On the other hand, the highest temperature of the day was recorded above 38°C in Metema, Gambella, Gewane and Awash Arba.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር አመች የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግኸምራ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ጉጂ ዞኖች፤ በአዲስ አበባ፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደራሼ እና ጌዲኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ ላሬ፣ ፉኝዶ፣ ጎዴ እና በቀብሪደሃር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, the favorable weather events for the formation of Belg rain will have better intensity across the northeast, central, southwest and southern parts of our country. In association with this, from Tigray region southeast, east and south zones; from Amhara region north and south Wollo, north Shewa, Waghemra and east Gojjam zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale and Guji zones; Addis Ababa; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta and Dawro zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadia, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; Sidama region zones, and from the Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Derashe and Gedeo zones will receive light to moderate amounts of rainfall. On the other hand, numerical forecast information shows that the maximum temperature of the day will exceed 38°C in Metema, Quara, Metekel, Pawe, Gambella, Lare, Fugnido, Gode, and Kebridehar.