Daily Weather Report 25 Mar 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በነቀምቴ፣ በበደሌ፣ በጋቲራ፣ በፉኚዶ፣ በአማን እና በዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፓዌ፣ በፉኝዶ፣ እና በላሬ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the country's western, south western, and southern parts. As a result, in Nekemte, Bedele, Gatira, Fugnido, Aman, and Dilla light to moderate rainfall was recorded. In contrast, the day's maximum temperature exceeded 38°C in Pawe, Fugnido, and Lare.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የደቡብ ምስራቅ ዞን፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ የየም ልዩ ዞን እና ሀድያ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ፓዌ፣ መተከል፣ ጋምቤላ፣ ፉኚዶ፣ ላሬ፣ ሰመራ፣ ገዋኔ እና ጎዴ ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማል፡፡
For the upcoming day, the west, southwest, south, central, and northeast portions of our country will have better cloud coverage. Along with this, from Tigray region southeast zone; from Amhara region west and east Gojjam, Waghemra, north and south Wollo zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west Wellega, west Arsi, north, west and southwest Shewa zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka and Kefa zones; from central Ethiopia region Gurage, Silte, Yem special zone and Hadiya zones and the Sidama region zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at some places. Conversely, numerical weather forecast information shows that the maximum temperature of the day will exceed 38°C in Humera, Metema, Pawe, Metekel, Gambella, Fugnido, Lare, Semera, Gewane, and Gode.