Daily Weather Report 25 Mar 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን የተስተዋለባቸው ሲሆን በጊዳያና፣ ነቀምቴ፣ አልጌ እና ቡሬ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ፉኝዶ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ40°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday Cloud cover was observed in the North-West, West and South-West parts of our country, and there was light rain in Gidayana, Nekemte, Alge and Bure. On the other hand, in Gambella, Fugnedo and Gode, the maximum temperature of the day was recorded above 40°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለበልግ ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የደቡብ ምስራቅ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ጉጂ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ ቋራ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ ጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ጎዴ እና ቀብሪደሃርላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Tomorrow the favourable weather events for the formation of Belg rain will strengthen in the northwest, northeast, central, southwest and south areas of our country. Along with this, the southeast, east and south zones of the Tigray region; North, Central and South Gondar, West and East Gojam zones from Amhara region; From the Oromia region of Jimma, Ilubabor, Guji and West Arsi zones; Sheka and Kefa zones of South West Ethiopia region and the Sidama region will receive light rainfall. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will be above 38°C in Metema, Quara, Metekel, Pawe, Gambella, Abobo, Lare, Gode and Kebridehar.